ድሬዳዋ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን አመሰገነች
/////////
የድሬዳዋ አስተዳደር ለታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር አካሒዷል።
ይህ የእውቅና ፕሮግራም ለ5ኛ ጊዜ የተካሔደ ሲሆን፣በመርሀ ግብሩ 17 የፕላቲየም፣41 የወርቅ፣50 የሲልቨር በአጠቃላይ 121 በላይ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ተመስግነዋል።
በዚህ የመድረክ የገቢዎች ሚኒስቴር ተወካዮች፣የድሮዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ባለሀብቶች፣የከተማዋ ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ሀገራቸውን በግንባር ቀደምትነት የምታገለግሉ፣በስራችሁ ውጤታማና ከግል ጥቅማችሁ ይልቅ የሀገርን ጥቅም የምታስቀድሙ በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባል ያሉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣እናንተ በምትከፍሉት ግብር ሀገር ትቆማለች፣የማህበራዊ አገልግሎቶችም ለህዝብ ተደራሽ ይሆናል ብለዋል።
እንደከንቲባው ገለፃ፣ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን የልዩ አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ እና በአስተዳደሩ በሚሰጡ አገልግሎቶች ሁሉ ቅድሚያ የሚያገኙበት ከእንግልት ነፃ ሆነው የሚገለገሉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል።
ድሬዳዋን ዘመናዊ፣ ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ለስራ ተስማሚ የማድረግ ራዕያችን ሙሉ በሙሉ የሚሳካው በበጎ አመለካከትና በተግባራዊ አጋርነት በመሆኑ፥ እስካሁን በአስተዳደራችን የተተገበሩት ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የስራ እድል ፈጠራና የማህበራዊ ድጋፍ ፕሮግራሞች እንዲሁም የዜጎችን ህይወት የሚያቀሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች በእናንተ የታማኝነት ግብር የተከናወኑ በመሆናቸው በእጅጉ ልትኮሩ ይገባል ነው ያሉት።
የገቢ መዋቅሩን በመፈተሽ ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ አድርገናል ያሉት አቶ ከድር ጁሀር፣ድሬዳዋን አልሙ፤ግብርን መሰወር ሀገርንና ህዝብን መካድ መሆኑን አስረድተዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር 13 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች እና 50ሺ ግብር ከፋዮች ይገኛሉ።
የህግ ተገዥነትን በማረጋገጥ ሒደት ውስጥ የድሬዳዋ አስተዳደር ጠቅላይ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ድርሻው ጉልህ ነው።በእለቱ የታክስ ንቅናቄው አካል የነበረውን "የአረንጓዴ አሻራ " መረሃ ግብርም በክቡር ካንቲባው መሪነት ሌሎች የአሰተዳድሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ከፍተኛ ግብር ከፋዬች በጋራ አካሄዷል 🌴🌿🍀።
"ግብር ለሀገር ክብር"

1 month ago