«ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ»፦ የኢትዮጵያ የመደመር ዲፕሎማሲ
*****************
«ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ» የሚለው መርህ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪካዊና አሁናዊ መሠረት ነው።
ኢትዮጵያ ይህን መርህ ከአፍሪካ ነፃነት ትግል ጀምሮ እስከ አሁኑ የዘመናዊ ዲፕሎማሲ ምዕራፍ ድረስ ይዛው ቀጥላለች።
የመደመር ዲፕሎማሲ የአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ችግሮቻቸውን በራሳቸው ውይይትና ባህላዊ እሴቶች መፍታት አለባቸው እንጂ የውጭ ኃይሎች መጫወቻ መሆን የለባቸውም የሚለውን ጽኑ እምነት ያንጸባርቃል።
በዚህም ኢትዮጵያ በታሪክ ከአፍሪካ ነፃነት ትግል ጀምሮ የነበራትን የመሪነት ሚና በመቀጠል፣ በአሁኑ ወቅት አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ለማስበር እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመመከትም ይህን መርህ በጽናት ትከተላለች።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው ድርድር ለዚህ እንደ ማሳያ ሆኖ ይነሳል። ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ወደ መንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እና ወደ አረብ ሊግ በመውሰድ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ጫና ለመፍጠር በሞከሩበት ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን ዕሳቤ በተግባር አውለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት እንዲካሄድ የያዙት አቋም ኢትዮጵያ ለሕብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር፤ ሀገራችን የአፍሪካ ችግሮች በባለቤቶቹ በአፍሪካውያን እንዲፈቱ ያላትን ጽኑ እምነትም ያረጋገጠ ነበር።
የአፍሪካውያንን ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ አንጻርም ኢትዮጵያ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን እና በሶማሊያ ግጭቶች በተከሰቱበት ወቅት የአፍሪካ ሕብረት እና የኢጋድ የሰላም ጥረቶችን በመምራትና የሰላም አስከባሪ ኃይል በማሰማራት አህጉራዊ ኃላፊነቷን ተወጥታለች።
ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስትሳተፍ፣ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን የአህጉራችንን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም የማስጠበቅ ሚናዋን ተግብራ እያሳየች ነው።
በዚህ ሁሉ የመደመር ዲፕሎማሲ ዕሳቤ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካም ዘብ የሚቆም ታላቅ ራዕይን የሰነቀ ዕሳቤ መሆኑን መመልከት ይቻላል።
በዓይናለም ሐድራ
#ethiopia #africa #medemer #diplomacy #ebc

2 months ago