ጋና አሜሪካን በመበለጥ በዓለም 6ኛዋ ከፍተኛ የወርቅ አምራች ሀገር ሆነች
ጋና አሜሪካን በመብለጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድስተኛዋ ከፍተኛ የወርቅ አምራች ሀገር ሆናለች።
ሀገሪቱ በ2025 እ.ኤ.አ ሪኮርድ የሆነ 185 ቶን (ወደ 5.94 ሚሊዮን አውንስ ገደማ) ወርቅ ያመረተች ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ ዕድገት በማሳየት ከአሜሪካ በላይ እንድትሰለፍ አድርጓታል።
የጋና ማዕድን ምክር ቤት ባልደረባ ክሪስቶፈር ኛርኮ እንደገለጹት፦ "አሁን ከፔሩ ቀጥሎ 6ኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን። ስለዚህ ቅደም ተከተሉ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፔሩ፣ ከዚያም ጋና... በመቀጠል አሜሪካ ይሆናሉ" ብለዋል።
ለዚህ የደረጃ ለውጥ አበይት ምክንያቶች ሁለት ናቸው። የጋና ምርት ያደገ ሲሆን፣ በአንጻሩ የአሜሪካ ምርት በኔቫዳ በሚገኙ የማዕድን ማውጫዎች ላይ ባጋጠሙ ቴክኒካዊ ችግሮች ምክንያት ቅናሽ አሳይቷል።
በጋና የ100 ዓመታት የንግድ ማዕድን ቁፋሮ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አነስተኛ አምራቾች ከሀገሪቱ ጠቅላላ የወርቅ ምርት ከ52 በመቶ በላይ የሚሆነውን አቅርበዋል።
በአንጻሩ ትልልቅ የማዕድን ኩባንያዎች ያመረቱት መጠን ካለፈው ዓመት በጥቂቱ ዝቅ ብሏል።
ለዚህ ስኬት ደግሞ በቅርቡ የተቋቋመው የጋና ወርቅ ቦርድ (GoldBod) ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ቦርዱ የኮንትሮባንድ ንግድን በመቀነስ ምርቱ በህጋዊ መንገድ ወደ ስርዓቱ እንዲገባ በማድረጉ፣ የአነስተኛ አምራቾች ወርቅ በመደበኛ መስመር ሊሰበሰብ ችሏል።
ጋና ከአፍሪካ አንደኛ የወርቅ አምራችነቷን ያስጠበቀች ሲሆን፣ ወርቅ አሁንም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ዋና ዋና ምርቶች መካከል ይጠቀሳል።
ይህ ለሀገሪቱ ትልቅና ታሪካዊ ክስተት ተደርጎ ተወስዷል።

2 months ago