Logo
Getu Temesgen
የሦስት ኮኮቦች ንትርክ

ይህ መጽሓፍ በሁለት የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ት/ቤት መምህራን የተዘጋጀ ፖለቲካዊ የሕይወት ምልከታ ነው።

ዶ/ር ኣርካ ኣቦታ ፅፎት፣ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው አሰናድቶታል፡፡ ብዙ ባልተነገረላቸው ባህላዊ ኣውዶችና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጓዝ መሳጭ ታሪክ ነው፡፡

የሦስት ኮኮቦች ንትርክ
#ethiopia | ባለቅኔና ጸሓፌ ተውኔት ፀጋዬ ገብረ መድኅን እንዳለው ሰው በሁለት መንገዶች ይማራል፤ “ኣንድም በሳር 'ሀ' ብሎ ኣልያም በኣሳር 'ዋ' ብሎ”፡ እኔ በሁለቱም ነው የተማርኩት፡፡

***

... በተለኮሱ ሙቃዳዎች ብርሃን፣ በእምቢልታ፣ በመለከት፣ በጃላዬና በኣጃቢዎቼ ፉከራ ደምቄ፣ …ወደ ሥፍራው ኣመራን። ግዝረቴ በቅጽበት ተፈፀመ።...

.… ሽመና ተምሬ ስሸምን ነበር…ከሞት ተርፌ ምናልባት እድሜ ልክ ከተፈረደብኝ እናቴን ወህኒ ቤት ሆኜ መርዳት እንደምችል ተስፋ ለማድረግ የበቃሁበት ሙያ ሆነ።

***

ከሞቶሎሚ የተወለደው የእግዚእ ኀረያ ልጅ ተክለ ሃይማኖት…ለክርስቲያናዊ ተልዕኮ የዘመተበት ቀዳሚ መድረሻውም የኣባቱ ኣገርና ግዛት ዎላይታ ይሆናል።

***

በጋብቻ የተሳሰሩና ብዙ ዕሴቶችን የተጋሩ ማኅበረሰቦች ሆነው... የጋራ ዕሴቶቻቸው ኣንዳቸው በሌላው ላይ የጭካኔ ተግባር እንዳይፈጽሙ ለምን ኣላገዷቸውም?...

***

ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን...

ከመጽሓፉ የተወሰዱ
ማራኪ አንቀጾች ናቸው።

***
የሦስት ኮኮቦች ንትርክ
ን - ፊደላሏ ጠቁራለች

ርዕሱን ደግመን ስናነበው
የሦስት ኮኮቦች ትርክት
የሦስት ኮኮቦች ንትርክ ይሆናል።

በነገራችን ላይ ...
ዶ/ር ኣርካ ኣቦታ እና ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ት/ቤት መምህራን ናቸው። እኔ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ደግሞ የሙያ ልጃቸው ነኝ።

ግልጽነት ለዘዘላለም ይኑር!
በዩኒቨርስቲው ውስጥ እኔን በዕውቀት፣ በሙያ ክሂሎትና በምግባርና ኮትኩቶ በየማሳደግ ረገድ ትልቅ ድርሻ አላቸው።

የዛሬውን ጌጡ ተመስገንን በዕውቀት አባትነት ወልደው ለዚህ አድርሰዋል።

"የሦስት ኮኮቦች ንትርክ" መጽሐፍ ጽፈው፣ አሰናድተው ለንባብ አብቅተዋል። በዚህም ( የቀለም ቀንድ) መሆናቸውን ዳግም በተግባር አስመስክረዋል።

በእጅጉም ኮርቻለሁ!
እጅም እነሳለሁ!
#ሼር #share

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.