(ዘ-ሐበሻ ዜና) የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ላይቤሪያ፣ ከአሜሪካ የተባረሩ የ"ሶስተኛ ሀገር" ስደተኞችን የመጀመሪያ ቡድን ሀሙስ ዕለት መቀበሏን የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። የላቲን አሜሪካ ስደተኞችን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ወደ 20 የሚጠጉ ስደተኞች ከአሜሪካ ከተባረሩ በኋላ ላይቤሪያ አርፈዋል።
ይሁን እንጂ ስደተኞቹን አሳፍራ የነበረችው አውሮፕላን ላይቤሪያ ከደረሰች በኋላ፣ ከስደተኞቹ መካከል ጥቂቶቹ ከአውሮፕላኑ አንወርድም በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸውን አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናግረዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግዳጅ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ ዳግም ወደ አውሮፕላኑ መመለሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን ያሉበት ሁኔታ በትክክል አልታወቀም።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ-ወጥ ስደትን ለመግታት እየወሰዱት ባለው ጠንካራ እርምጃ እና ስደተኞችን ምንም ዓይነት ትስስር ወደሌላቸው "የሶስተኛ ሀገራት" ለማባረር ኋይት ሀውስ በጀመረው ዘመቻ መሰረት፣ ዜጎቿ ያልሆኑ ስደተኞችን የተቀበለች የቅርብ ጊዜ ሀገር ላይቤሪያ ሆናለች። የላይቤሪያ መንግስት በቀጣዩ ዓመት ከአሜሪካ የሚባረሩ እስከ 1,200 የሚደርሱ የሶስተኛ ሀገር ስደተኞችን ለመቀበል ማቀዱን እና አዲስ መጪዎቹም በሀገሪቱ የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል። በዚህም መሰረት የትራምፕ አስተዳደር ባለፈው ዓመት በስህተት ወደ ኤልሳልቫዶር ተባርሮ ወደ አሜሪካ የተመለሰውን ኪልማር አብሬጎ ጋርሲያ የተባለውን ግለሰብ ወደ ላይቤሪያ ለማባረር እየሞከረ መሆኑ ተጠቁሟል።
የትራምፕ አስተዳደር በታጠቁ ግጭቶች፣ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና በሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከሚታመሱት ደቡብ ሱዳን፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ካሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ጋር የሶስተኛ ሀገር የስደተኞች ስምምነቶችን ተፈራርሟል።
ጋና፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በተመሳሳይ ከሌሎች ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማምተው መደበኛ የማባረር በረራዎችን እያስተናገዱ ይገኛሉ።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይህንን የሶስተኛ ሀገር የስደት ማስወጣት እርምጃ ኢ-ሰብአዊ እና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ህገ-ወጥ ነው ሲሉ አውግዘውታል። በተለይም አንዳንዶቹ ሀገራት ስደተኞቹን ከጭቆና ወደ ሸሹበት ሀገር መልሰው ሊልኳቸው ይችላሉ የሚል ከባድ ስጋት አላቸው። በአንጻሩ የትራምፕ አስተዳደር እርምጃው ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል ውጤታማ መንገድ ነው በማለት ህጋዊነቱንና ጠቀሜታውን ይሟገታል። በአብዛኛው ይህ የአስተዳደሩ ጥረት ያነጣጠረው የትውልድ ሀገራቸው ከአሜሪካ የሚባረሩ ዜጎቻቸውን በማይቀበሉ ወይም ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ ህጋዊ ጥበቃ ባገኙ ስደተኞች ላይ ነው።

2 months ago