Logo
Getu Temesgen

ግራንድ አፍሪካን ረን በዲሲ
ከሩጫም በላይ ነው። ኦክቶበር 10 ጠዋት

በ8ኛው ዓመት የግራንድ አፍሪካን ረን ሲሳተፉ የመረጡትን አንድ በጎ ዓላማ ማገዝ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በልብ ህክምና፣ በካንሰር ህመም፣ በኦቲዝም፣ የሴት ልጆችን በማገዝ፣ እና በህፃናት ትምህርት ዘርፍ፤
በዘንድሮው ዝግጅት አስር የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እገዛ የሚፈልጉ ወገኖቻችንን ለመደገፍ ከግራንድ አፍሪካን ረን ጋር ኣብረው ይሰራሉ።

እርሶም ከቤተሰብዎ፣ ከወዳጅ ዘመድዎ፣ እና ከወገንዎ ጋር በዝግጅቱ ላይ ከሚያሳልፉት አስደሳች የአብሮነት ጊዜ ባሻገር፤
አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና ዓላማ መርጠው ሲሳተፉ የ5% ቅናሽ መመዝገቢያዎ ላይ ያገኛሉ ።

የሚደግፉት ኣንድ ዓላማን ለመምረጥ ከዚህ መልዕክት ጋር የማስቀምጥላችሁን ድረ፡ገጽ ይመልከቱ።

በዚህ የቤተሰብዎ የሆነ ዝግጅት፣ ለአዋቂዎች የ5ኪ.ሜ እና ለህፃናት የ1ኪ.ሜ በርምጃ፣ በሶምሶማ፣ አሊያም በሩጫ የሚካፈሉበት ዝግጅት ተሰናድቷል።

ርቀቱን አንደኛም ሆነ መጨረሻ ቢያጠናቅቁ፣ የ2026 ቶዮታ ኮሮላ ለተሳታፊዎች በሎተሪ ዕጣ እንደሚቀርብ አይዘንጉ ።

እርሶም ቤተሰብዎን፣ ጏደኛዎን፣ የስራ ባልደረባዎን ይዘው፣ በዚህ ዝግጅት እንዲሳተፉ አንጋብዝዎታለን።

ለመመዝገብ ድረ-ገጹን ይጠቀሙ
www.africanrun.com
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.