የብሪክስ ሀገራት በቴክኖሎጂ እና በፋይናንስ ትብብር ግዙፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ እንደሚችሉ አዲስ ጥናት አመለከተ
******************
የብሪክስ አባል አገራት በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያሳዩት ፈጣን እድገት ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (GDP) በ656 ቢሊዮን ዶላር ማሳደግ እንደሚችል አዲስ የወጣ ጥናት አመለከተ።
በተጨማሪም በአባል አገራቱ መካከል ያለው ጠንካራ ትብብርና ቅንጅት ከ2.7 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም እንደሚፈጥር ተጠቅሷል።
ይህ ጥናት የሩሲያ የገንዘብ ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን፣ በቅርቡ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መድረክ ላይ ይፋ ሆኗል።
የፋይናንስ መሠረተ ልማቶችን ማቀናጀትና የካፒታል ገበያን ማሳደግ ለአገራቱ የኢኮኖሚ እድገት ዋነኛ ተስፋዎች እንደሆኑ በጥናቱ ተመላክቷል።
አባል አገራቱ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቻቸውን የገበያ እሴት ለማሳደግና ባለሃብቶች በጋራ የገበያ መድረኮች እንዲሳተፉ ለማስቻል በትኩረት እየሰሩ ይገኛሉ።
አማራጭ የፋይናንስ ገበያ ስርዓቶችን መዘርጋት ብቻውን በየዓመቱ እስከ 12 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ተጨማሪ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚያስገኝ የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
በሰለሞን ገዳ
#brics #economicgrowth #techinnovation #financialcooperation #globaleconomy

2 months ago