Logo
Getu Temesgen
ኮንጎ ለኤሎን መስኩ ተቋም ፍቃድ ሰጠች!
#ethiopia |የኤርቴል አፍሪካ እና የኢሎን መስክ ስታርሊንክ በጋራ በመሆን የመጀመሪያውን የሳተላይት ስልክ አገልግሎት አስጀመሩ።

ሁለቱ ተቋማት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሳተላይት ስልክ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል።

ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ የቴሌኮም ማማዎች በሌሉባቸው ወይም የኔትወርክ ሽፋን ባልደረሰባቸው ገጠራማ አካባቢዎች የሚተገበር ነው።

አገልግሎቱ የኤርቴል ደንበኞች ስልካቸውን በቀጥታ በህዋ ላይ ከሚገኙ የስታርሊንክ ሳተላይቶች ጋር እንዲያገናኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ የጽሁፍ መልእክቶችን እና እንደ ዋትስአፕ ያሉ ቀላል መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ያስችላል።

ሁለቱ ተቋማት ባደረጉት የአጋርነት ስምምነት መሠረት ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እየሰፋ ሲሄድ የድምፅና የቪዲዮ ጥሪዎችን ጨምሮ ተጨማሪ የዳታ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ተስማምተዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #airtelafrica #elonmusk #starlink #technology #congo

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.