የመንግሥት ሥርዓት ባህሪያት፦ ፓርላማዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ?
በአለምአቀፍ እና በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ
በፋንታሁን ደለለው - Lawyer
መግቢያ #ethiopia | መንግስታት ሀገራቸውን የሚያስተዳድሩበት የራሳቸውን ስረአተ መንግስት ይከተላሉ። በአለም ላይ በዋናነት የታወቁት እና በተግባር የሚታዩት ፓርላማዊ/Parliamentary/እና ፕሬዚዳንታዊ /presidential/ናቸው።
ፓርላማዊ እና ፕሬዚዳንታዊ ስረአተ መንግስት የተለያየ አይነት የመንግስት ስረአት ሲሆኑ የስረአቱ መቀያየር በመንግስቱ አወቃቀር ከላይ እስከ ታች ድረስ የተለያየ የተለያየ ባህሪ እንዲኖረው የሚያደርገው ሲሆን በዚህ ጽሁፍ ፓርላሜንታዊ ስረአት መንግስት ምንድነው? ፕሬስደንሼያል ስረአተ መንግስት ምንድነው? የእኛ የኢትዮጵያ ስረአተ መንግስት ምን ይባላል? ለእኛ አይነት ሀገርስ የትኛው አይነት ስረአተ መንግስት ይመከራል? የሚሉት ነጥቦችን በመዳሰስ ለአንባቢው ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይህንን ጹሁፍ ወደ እናንተ አቅርበናል።
1. ስረአተ መንግስት ምንድነው?
ስረአተ መንግስት ማለት መንግስት የሚመራበት ስረአት ማለት ሲሆን በዋናነት በአለማችን ላይ ሁለት አይነት ስረአተ መንግስት ይገኛሉ። እነርሱም ፓርላሜንታዊ እና ፕሬስደንሽያል ስረአተ መንግስት ሲሆኑ የእነዚህ ቅይጥ ስረአት መንግስት እንዳለም ይታወቃል። በዚህ ጽሁፍ በዋናነት ሁለቱን የፕሬስዳንሻል እና የፓርላሜንታሪ ስረአተ መንግስት ትኩረት የየምናደርግበት ነው። እነዚህ ስረአቶች ገዢው መንግስት ተገቢና አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ የሀገሩን ባህሪ፣የህዝቡን ሁኔታ፣የሀገሪቱን እድገት፣ የውጭ ግንኙነት ያሰበውን ከሀገራዊ ፋይዳና ራእይ አንጻር የትኛው ሊጠቅም እንደሚችለው በመለየት በየትኛው ስረአተ መንግስት መምራት እንዳለበት ወስኖ ሀገርን የሚመራበት ስረአት ፥ ስረአት መንግስተ ይባላል።
2. ሁለቱ ስረአተ መንግስቶች መሠረታዊ ባህሪያቸው ምንድን ነው?
2.1 የመንግስት ምስረታ በፓርላሜንታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት
ፓርላሜንታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በዋናነት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ስልጣን ባለቤት የሚሆንበት ስርዓት ነው፡፡ በዚህ አይነት የመንግስት ስርዓት ውስጥ የመንግስት ምስረታ የተለያዩ ሂደቶች ሊኖሩት ይችላል፡፡ ይህ ማለት በተለያዩ የህግ ስርዓቶች ውስጥ የመንግስት ምስረታ ወይም የመሪዎች ምርጫ የተለያየ ሂደት አለው፡፡
በዚህ መሰረት በአንዳንድ ሀገራት ጠቅላይ ሚኒስትር በሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሚሰየም ሲሆን በሌሎች ሀገራት የህግ አውጪው አካል ጠቅላይ ሚኒስትርን የሚመርጥበትን ሂደት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሌሎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ከህግ አውጪው አካል የሚመረጡበትን አሰራር የሚከተሉ ሀገራት ያሉ ሲሆን አንዳንድ ሀገራት ህግ አውጪው እና ህግ አስፈፃሚው አካል መለያየት ስለሚገባቸው እነዚህ ሚኒስትሮች ከህግ አውጪው መመረጥ የለባቸውም የሚል አቋም ይይዛሉ፡፡ ሌሎች ሀገራት የቅልቅል ሂደትን የሚከተሉ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሌሎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ከህግ አውጪው አካል ወይም አባል ካልሆኑ ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ሀገራት እንደሚከተሉት ስርዓት በጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾሙ ወይም በጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት በርዕሰ ብሔር ወይም በህግ አውጪው አካል ሊሾሙ ይችላሉ፡፡ ይህም ብዙ ጊዜ በሚስጥር በሚደረግ ሳይሆን በግልፅ ምርጫ የሚደረግ ነው፡፡
2.1.1ፓርላማዊ ስርአተ መንግስት ጥንካሬ
ሀ. ይህ ስረአት ዲሞክራሲ በጣም ባልዳበረበቸው ሀገራት እንደ አፍሪካ እና ምስራቅ እሲያ ሌሎችም እነዚህን በመሳሰሉት ሀገራት የሚመከር ነው። አስፈጻሚው አካል የምክር ቤት አባል የሚሆንበትን ባህሪ ያሳያል። የዚህ ስረአተ መንግስት አንዱና ዋነኛ ጠቀሜታው የመንግሥትን ፖሊሲ፣ተልእኮ፣ህገመንግስቱን አስጠብቆ ለማስኬድ ከፍተኛ እድል ይፈጥርለታል።
ለ. አስፈጻሚው አካል ማለትም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ወይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርባቸውን ረቂቅ አዋጅ ፣ የአለምአቀፍ ስምምነቶችን ለማጸደቅ ከፍተኛ እድል ይፈጥራል።
ሐ. የገዢው መንግስትን የፖለቲካ ድርጅት ለማጠናከርና በምክር ቤቱ የሚነሱ ሀሳቦችን በበላይነት ለማስኬድ የሀገሪቱን አጠቃላይ አካሄድ ለመቆጣጠር ከፍተኛ እድል ይፈጥርለታል።
መ. ለያዘው ስረአተ መንግስት የሚመቹ አመራሮችን ዳኞችን የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ ለመሾም ለመንግስትነት አካሄዱ ካልተመቸውም ለመሻር እድል ይፈጥርለታል።
ሠ. አስፈጻሚው ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ መሆኑ ለተጠያቂነትና ግልጸኝነት አሰራር አመቺ መንገድን የሚፈጥር ነው።
ረ. ጠቅላይ ሚኒስተሩ አስፈጻሚዎችን የመሾም ስልጣን መኖሩ ለአስተዳደሩ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።
2.1.2 የሚተችበት ደካማ ጎን
ሀ. የስልጣን ክፍፍል/separation of power/
የስልጣን ክፍፍል በሶስቱ የመንግስት ክፍሎች በተለየ ሁኔታ/clearly/ የለም ተብሎ ይተቻል። እራሱ አስፈጻሚ ሆኖ ህግ አውጪ መሆኑ የስልጣን ክፍፍልን ትርጉም የሚያሳጣው በመሆኑ የዲሞክራሲያዊ ባህሪን ሙሉነት የሚያሳጣው ነው ተብሎ ይተቻል።
ለ. የቁጥጥር ስረአት/check and balance/
የመንግስት አካላት የሆኑት አስፈጻሚው፣ህግ አውጪው፣ህግ ተርጓሚው እርስ በእርሳቸው ቁጥጥር የሚደረግበት ስረአት የላላ በመሆኑ ዲሞክራሲን የሚያጠናክር አይደለም ተብሎ ይተቻል።
ሐ. የስልጣን መቀላቀል
ህግ አስፈጻሚው በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህግ አስፈጻሚም ሆነ በህግ አውጪው/በምክር ቤቱ / ቦታ መቀመጫ/ስልጣን/ በመኖራቸው ስልጣንን/power/ የመጠቅለል ባህሪ ስለሚኖረው የመንግስት አሰራርና ተጠያቂነትን መርህ ስጋት ውስጥ የሚከት ነው ተብሎ ይተቻል።
መ. የህግ አስፈጻሚው የእድሜ ዘመን የህግ አውጪ እድሜ ዘመን ነው። ህግ አስፈጻሚው ከህግ አውጪው የተለየ አይደለም።
3. የፕሬዚዳንታዊ ስርአተ መንግስት/ presidential government / ባህርያት
ይህ ስረአተ መንግስት የስልጣን ክፍፍል/separation power/ የሚታይበት ሲሆን የሀገር መሪው/Head of government/ ከምክር ቤቱ ወይም አብላጫ ወንበር ከያዘው የፖለቲካ ድርጅት የሚመረጥ ሳይሆን ዜጎች በምርጫ የሚመርጡት ነው። ፕሬዝዳንቱ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ሳይሆን ለህዝብ ነው። ፕሬዝዳንቱ የምርጫ ዘመኑ ውስን ሲሆን የህግ አውጭውን የምርጫ ዘመን የሚከተል አይደለም። ያለበት የፖለቲካ ድርጅት በምክር ቤቱ አብላጫ ወንበር ያዘም አልያዘም በዜጎች የሚመረጥ በመሆኑ ከዚህ ጋር የሚያገናኘው የለም።
3.1 የፕሬስዴንሽያል ስረአተ መንግስት/ presidential government / ጥንካሬው
ሀ.. የስልጣን ክፍፍል/separation of power/
በአስፈጻሚው፣በህግ አውጪው፣በህግ ተርጓሚው መካከል ግልጽና የተለየ ነው። አስፈጻሚው ህግ አውጪ አይደለም።
ለ. የቁጥጥር ስረአት/check and balance/
ሶስትም የተለዩ አንዱ የሌላውን ስልጣን የማይቆናጠጥ በመሆኑ (ለምሳሌ አስፈጻሚው የህግ አውጪውን የማይዝ ) አንዱ አንዱን ለመቆጣጠር አመቺ ነው።
ሐ. ፕሬዝዳንቱ የሚመረጠው ቀጥታ በዜጎች ድምጽ መሆኑ
ፕሬዝዳንቱ ሀገር ለመምራት የሚያስችለው አቅም ያለው ስለመሆኑ በገር ወዳደድነቱ፣በብቃቱ ፣ በምግባሩ፣በፖለቲካ ብስለቱ በመሳሰሉት ዜጎች ቀጥታ አይተው መዝነው የሚመርጡበት እንጂ እንደ አሸናፊ ፖለቲካ ፓርቲ የፖለቲካው አባላት እራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመረርጡበት አይደለም።
መ. ፕሬዝዳንቱ አስፈጻሚዎችን የመሾም ስልጣን መኖሩ ለአስተዳደሩ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
3.2. ድክመት
ሀ. የፕሬዝዳንቱ ፖለቲካ ፓርቲ የተሸነፈ እንደሆነ በህግ አውጪው ምክር ቤት ከሚፈልገው ፖሊሲ አንጻር ሊያጸድቅ የሚፈልገው ህግ የመጽደቁ እድል የጠበበ ነው።
ለ. አስፈጻሚው የሚበጀውን ህጎች ለማጸደቅ በምክር ቤት ድምጽ የመስጠት እድል የለውም
ሐ.ፕሬዝዳንቱ ለምክር ቤት ተጠሪ ባለመሆኑ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንቱን የመቆጣጠር እድል ያነሰ ይሆናል።
መ.በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በቀር ፕሬዝዳንቱ እና አስፈጻሚው ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ባለመሆኑ ለቁጥጥር ልልነት በር ከፋች ሊሆን ይችላል።
4. ስረአተ መንግስት በኢትዮጵያ ያለው ባህሪያት
ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ስረአት ፓርላሜንታሪ ዲሞክራሲያዊ እንደሆነ በሀገራችን ህገ መንገስት አንቀጽ 45 ላይ ተደንግጓል፡፡ የፌዴራል ፓርላማ በሁለት ምክር ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን እነዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደረሽን ምክር ቤት ናቸዉ፡፡ ሁለቱም ምክር ቤቶች የተለያየ አወቃቀር፣ ሥልጣንና ተግባር እንደላቸዉ በሕገመንገስቱ ተደንግጓል፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 8 መሠረት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የሥልጠን ባለቤት መሆናቸዉን ይደነግጋል፡፡ ሉዓላዊነታቸዉ የሚገለጸዉ በህገ-መንግስቱ መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮች ወይም በቀጥታ በሚደረግ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካይነት መሆኑን በዚሁ አንቀጽ ስር ተደንግጓል፡፡ በህገ መንግስታችን መንግስት ስንል የህግ አዉጪዉን፣ ህግ አስፈፃሚዉን እና ህግ ተርጎሚ አካሉን በአንድ ላይ የያዘ ነዉ፡ መሆኑ ይታወቃል። በህግ መንግስቱ አንቀጽ 50 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በፌዴራል እና በክልሎች የተዋቀረ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ስር የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የፌዴረል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም የህግ አዉጪዉ እንደሆነ እና የምክር ቤቱ ተጠሪነትም ለህዝቡ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡ በተመሳሳይ በክልሎችም ከፍተኛ የሥልጣን አካል የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም የህግ አዉጪዉ እንደሆነ እና የምክር ቤቱ ተጠሪነትም ለህዝቡ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡
መንግስትን ማቋቋም የሚቻልበትን በተመለከተ የመንግስት ስልጣን በምርጫ ብቻ እንደሚያዝ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 9 (3) ይገልፃል፡፡ እንዲሁም በአንቀፅ 56 እና 73 (2) እንደተገለፀው በምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘ ፓርቲ መንግስትን ይመሰርታል፡፡
የምስረታ ሂደት እና መሪዎቹ የሚመረጡትን መንገድ በተመለከተ የህግ አውጪው አካል (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) አባላት በፓርቲዎች አቅራቢነት በምርጫ በህዝብ ተመርጠው የምክር ቤቱ አባል እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ ግን ከምክር ቤቱ አባላት መካከል በምክር ቤቱ እንደሚመረጡ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 (19) ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በክልሎች ምክር ቤቶች ተመርጠው እንደሚላኩ አንቀፅ 61 (3) ላይ የተገለፀ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አባላት መካከል በምክር ቤቱ ይመረጣሉ፡፡
የህግ አስፈፃሚ አካል ምርጫን በተመለከተ የህግ አውጪው አካል (ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) የህዝብ ተወካይ በመሆኑ በህግ አስፈፃሚው እና ህግ ተርጓሚው አካል ምርጫ ላይ ትልቅ ስልጣንና ተሳትፎ አለው፡፡ በዚህ መሰረት የሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢነት ሁለቱ ምክር ቤቶች (በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት) በጋራ የሚመርጡ መሆኑን አንቀፅ 70 ይደነግጋል፡፡ ርዕሰ ብሔር ከምክር ቤቱ አባላት ወይም አባል ካልሆኑት ውስጥ ሊመረጥ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በህግ አውጪው አካል (በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) እንደሚመረጡ አንቀፅ 55 (19) ያሳያል፡፡ እንደ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 73 (1) መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል የሚመረጥ ሲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ወይም አባል ካልሆኑ ሰዎች ሊመረጡ እንደሚችሉ ከአንቀፅ (74 (3) መረዳት ይቻላል፡፡
የህግ ተርጓሚ አካል ወይም ፍርድ ቤትን በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት በጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚመረጡ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 (13) ላይ ተገልፆል፡፡ በተመሳሳይም የሌሎች ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች እና ዳኞችም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት እንደሚሾሙ በህጉ ተደንግጓል፡፡ የክልል መንግስታትም በተመሳሳይ የራሳቸውን መንግስት በህገመንግስቱ አንቀጽ 50 መሠረት በግልጽ ተደንግጓል።
5. ማጠቃለያ
በአለማችን ላይ በዋናነት ሁለት አይነት ስረአተ መንግስት/form of the government/ ያሉ ሲሆን እነዚህም ፕሬስዴንሽያል/Presidential/ እና ፓርላመንተራዊ/ Parliamentary/ስረአት መንግስት በመባል የሚታወቁ ናቸው። እነዚህም እያንዳንዳቸው በመንግስት አወቃቀር፣በምርጫ ስረአት፣በስልጣን ክፍፍል፣በመንግስት ተጠሪነት፣በቁጥጥር ስረአት የራሳቸው ባህሪያት ያላቸው ሲሆን ኢትዮጵያ በኢፊድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 45 መሠረት ፓርላሜንታዊ ስረአተ መንግስትን ትከተላለች።
ማጣቀሻዎች
1. የኢፊድሪ ህገመንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987
2. የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስተር ድረ ገጽ
3.SYSTEMS OF GOVERNMENT
Denis Baranger and Christina Murray
4. Others International papers/documents/Researches on forms/system of government
https://www.facebook.com/s...
https://t.me/Fantahunlawye...

2 months ago