Logo
Getu Temesgen
በምእመናን እና በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተዘግታ የቆየችውን ቤ/ክ ዳግም ለመክፈት ውይይት ተደረገ
#ethiopia | ​ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር አንቶኒዮስ ስጉሮፖሎስን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የውይይቱ ዋና ትኩረት በግሪክ አቴንስ ከተማ የምትገኘውና ከ40 ዓመታት በላይ አገልግሎት ስትሰጥ የነበረችው የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበት ሁኔታና ወደ አገልግሎት የምትመለስበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነው።

​ይህች ታሪካዊ ቤተክርስቲያን በምእመናን እና በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በሀገሪቱ የሃይማኖት ሚኒስቴር ትእዛዝ አገልግሎቷ ተቋርጦ የተዘጋች ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንደገና ተከፍታ አገልግሎት የምትጀምርበት አካሄድ ተመክሮበታል።

​ቤተክርስቲያኗ በስደት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባለፈ ባህልና እምነትን ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መጠጊያ ለመሆን የምታደርገው በጎ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የተፈጠረው ችግር ተፈትቶ አገልግሎቱ በፍጥነት እንዲቀጥል ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

EOTC BSA

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.