Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን (ENDC) የተቋቋመበት ህጋዊ ሥልጣን ፣ የውሳኔ ሰጪነት እና ተፈጻሚነት
በኢትዮጵያ ህጋዊ ማእቀፍ

መግቢያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን (ENDC) በይፋ የተቋቋመው በታኅሣሥ 20/ 2014 ዓ.ም. (በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 29፣ 2021) በአዋጅ ቁጥር 1265/2014/ መሆኑ ይታወቃል። አዋጁ ከጸደቀ ከሁለት ወራት በኋላ፣ በምክር ቤቱ የተመረጡት 11 ዋና ኮሚሽነሮች ቃለ-መሐላ ፈጽመው በይፋ ሥራ የጀመሩት በየካቲት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. (የካቲት 21፣ 2022) መሆኑን ካገኘነው መረጃ የተረዳን ሲሆን በዚህ ጹሁፍ የኮሚሽኑ አጠቃላይ ስልጣን ፣ የውሳኔ ሰጪነት ገደብ እና ተፈጻሚነት እንዲሁም ኮሚሽኑ ለመቋቋም የህግ መሠረት ፣ እንዲሁም በኮሚሽኑ ምክረ ሀሳብ ላይ የመንግስት ወይም አስፈጻሚ አካሉ የማስፈጸም ግዴታ እነ በዚህ ላይ የኢፊድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለው ስልጣን ምን እንደሆነ የህግ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የቀረበ ጽሁፍ ነው።

1. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን (ENDC) ህጋዊ ስልጣን
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን (ENDC) የፖለቲካ ውሳኔዎችን የመወሰን ወይም ሕግ የማውጣት ቀጥተኛ የመንግሥትነት ሥልጣን የለውም። ነገር ግን ሂደቱን በበላይነት ለመምራት የሚያስችለው ሙሉ አስተዳደራዊ እና ሥነ-ሥርዓታዊ የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣን በአዋጅ ተሰጥቶታል።የኮሚሽኑ የውሳኔ ሥልጣን ይዘት፣ በአዋጅ የመቋቋሙ ሕጋዊ መሠረት እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ተቋም ለማቋቋም ያለው የሕግ ምንጭ እንደሚከተለው ነው።

. የኮሚሽኑ የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣን ምንነት በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሠረት ኮሚሽኑ በሚከተሉት የሥራ ክፍሎች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ያለው ሲሆን እንደሚከተለው ቀርቧል።

1.1. የአጀንዳዎች ውሳኔ፦ ከሕዝብና ከባለድርሻ አካላት የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን መርምሮ፣ የትኞቹ ለአገራዊ ምክክር እንደሚቀርቡ የመወሰን ሥልጣን

1.2. የተሳታፊዎች ልየታ ውሳኔ፦ በማንኛውም የምክክር መድረክ ላይ እነማን መሳተፍ እንዳለባቸው የመወሰን እና የማጽደቅ ሥልጣን

1.3. የምክረ-ሐሳብ ይዘት ውሳኔ፦ በምክክሩ ማጠቃለያ ላይ ወደ መንግሥት የሚላኩትን የመጨረሻ "የምክረ-ሐሳብ ሰነዶች" ይዘትና አወቃቀር የመወሰን ሥልጣን

1.4. የውስጥ መዋቅርና አደረጃጀት ውሳኔ፦ የኮሚሽኑን የውስጥ መመሪያዎች ማውጣት፣ ክልላዊ ጽሕፈት ቤቶችን መክፈት እና አወያዮችን የመሰየም ሙሉ ሥልጣን

2. በአዋጅ ለመቋቋሙ የሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን ምንጭ
የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት ለማንኛውም የፌዴራል ሕግ ወይም ተቋም መቋቋም የበላይ የሕግ ምንጭ ነው። የዚህ ኮሚሽን በአዋጅ መቋቋም የሚከተሉትን ሕገ-መንግሥታዊ መርሆዎች መሠረት ያደርጋል፦

2.1. ሕገ-መንግሥታዊ ዋስትና (የሰላምና አንድነት ግዴታ)፦ በሕገ-መንግሥቱ መግቢያ (Preamble) እና በተለያዩ ድንጋጌዎች ላይ የሕዝቦችን ሰላም፣ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እና ሕጋዊ ሥርዓትን የማስከበር ኃላፊነት ለመንግሥት ተሰጥቷል። ይህንን ትልቅ ብሔራዊ ግብ ለማሳካት መንግሥት ጊዜያዊ ወይም ቋሚ የሆኑ ልዩ ተቋማትን በአዋጅ ማቋቋም ይችላል።

2.2. የሕግ የበላይነት መርሆ (አንቀጽ 9)፦ ሕገ-መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ በመሆኑ፣ ማንኛውም ተቋም ሲቋቋም ሕጋዊ ሰውነት እንዲኖረውና ከሕገ-መንግሥቱ ጋር የማይጋጭ ግልጽ አዋጅ ሊወጣ እንደሚገባ የሚደነግግ ሲሆን ይህን መሠረት ያደረገ ነው።

3. የምክር ቤቱ (የፓርላማው) የሕግ ምንጭና ሥልጣን...
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማው) ይህንን ኮሚሽን በአዋጅ ለማቋቋም ያለው ግልጽ የሕግ ምንጭ የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ነው። በዚህ ድንጋጌ ሥር የተዘረዘሩት የምክር ቤቱ ሥልጣናት የሚከተሉትን ተቀምጧል።

3.1. አጠቃላይ ሕግ የማውጣት ሥልጣን (አንቀጽ 55/1)፦ ምክር ቤቱ በሕገ-መንግሥቱ ለፌዴራሉ መንግሥት በተሰጡት የስምሪት ዘርፎች (በተለይም ሀገራዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና የሕግ የበላይነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች) ላይ ሕግ የማውጣት ሙሉ ሥልጣን አለው።

3.2. ገለልተኛና ገዢ ተቋማትን የማቋቋም ሥልጣን፦

4. የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኮሚሽኑን ከማቋቋም እና ሌሎች በዚህ ላይ ከህግ አንጻር ያለው የስልጣን ምንጭ...

1. ኮሚሽኑን የማቋቋም ህጋዊ ስልጣን

ምክር ቤቱ ተጠያቂነታቸው ቀጥታ ለራሱ የሆኑ (እንደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ዕንባ ጠባቂ እና ምርጫ ቦርድ) ተቋማትን የማቋቋም ሕገ-መንግሥታዊ ልምድና ሥልጣን አለው።

2. ኮሚሽኑን የስራ ተግባሩን የመከታተል ስልጣን

2.1. ተጠሪነት

የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽንም በተመሳሳይ መልኩ ተጠያቂነቱ ለምክር ቤቱ ሆኖ የተቋቋመው በዚህ ሥልጣን መሠረት ነው።

2.2. አስፈጻሚ አካላትን የመቆጣጠር ሥልጣን፦

ምክር ቤቱ ሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታት እንዲረዳው አስፈጻሚውን አካል ያላካተተ፣ ራሱን የቻለና በገለልተኝነት የሚሠራ ኮሚሽን የመሰየም ሙሉ የሕግ መብት አለው።በመሆኑም ኮሚሽኑ የመንግሥትን የዕለት ተዕለት ሥራ የመወሰን "የአስፈጻሚነት ሥልጣን" ባይኖረውም፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን (በአንቀጽ 55 መሠረት) በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 የተሰጠው የሂደት መሪነትና የምክረ-ሐሳብ አውጪነት ሙሉ ሕጋዊ ሥልጣን አለው።

2.3. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የውሳኔ ሀሳቦች አስገዳጅነት

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን (ENDC) በምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የሚያቀርባቸው የውሳኔ ምክረ-ሐሳቦች ወደ መንግሥት ከሄዱ በኋላ ያላቸው ሕጋዊ አስገዳጅነት ቀጥተኛ አይደሉም።(Institutional and Procedural Obligation) ነው [1265/2014]

ይህ ማለት በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሠረት መንግሥት ምክረ-ሐሳቦቹን በቸልታ የመተው ወይም የመጣል መብት የለውም፤ ነገር ግን ምክረ-ሐሳቦቹ በቀጥታ እንደ ሕግ ተፈጻሚ አይሆኑም።

የምክር ቤቱ (የፓርላማው) የመቀበልና የመምራት ግዴታኮሚሽኑ የመጨረሻውን የምክረ-ሐሳብ ሰነድ የሚያቀርበው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው ።

ሀ. አዋጁ ለምክር ቤቱ የሚከተሉትን ሕጋዊ ግዴታዎች ጥሏል፦
ሰነዱን የመቀበልና የመወያየት ግዴታ፦ ምክር ቤቱ ከኮሚሽኑ የሚቀርቡለትን የብሔራዊ መግባባት ምክረ-ሐሳቦች ተቀብሎ የመወያየትና የመመርመር ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት።

ለ. ለአስፈጻሚ አካላት የመምራት ግዴታ፦ ምክር ቤቱ የቀረቡትን ምክረ-ሐሳቦች መርምሮ፣ ውሳኔዎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ለአስፈጻሚው የመንግሥት አካል (ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም ለሚመለከታቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች) በይፋ ይመራል።

የአስፈጻሚው አካል (የመንግሥት) የመተግበር ኃላፊነት ምክር ቤቱ የመጨረሻውን ሰነድ ካጸደቀውና መመሪያ ከሰጠ በኋላ፣ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል የሚከተሉትን እርምጃዎች የመውሰድ ሕጋዊና ፖለቲካዊ ግዴታ አለበት፦

ሐ. ወደ ሕግና ፖሊሲ የመቀየር ኃላፊነት፦ ምክረ-ሐሳቦቹ ተግባራዊ መሆን የሚችሉት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ነው። ለምሳሌ፦ የምክክሩ ውጤት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያን፣ የአዳዲስ ሕጎችን መውጣት ወይም የፖሊሲ ለውጦችን የሚጠይቅ ከሆነ፣ መንግሥት እነዚህን የሕግ ማዕቀፎች የማዘጋጀትና የመቅረጽ ግዴታ አለበት።

መ. የበጀትና የሰው ኃይል የመመደብ ግዴታ፦ በምክክሩ የተደረሱ ስምምነቶችን መሬት ለማውረድ መንግሥት አስፈላጊውን በጀትና የአፈጻጸም መዋቅር የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት።

3. የኮሚሽኑ የክትትልና የማስገደጃ ሥልጣን

አዋጁ ኮሚሽኑ ምክረ-ሐሳቦቹን ከላከ በኋላ የሚተወው ሳይሆን ይልቁንም የክትትል ሥልጣን ሰጥቶታል። የአፈጻጸም ክትትል ሥርዓት አስመልክቶ ኮሚሽኑ የላካቸው ምክረ-ሐሳቦች በመንግሥት አካላት እየተተገበሩ መሆኑን የመከታተል ሕጋዊ ሥልጣን አለው ለፓርላማ ሪፖርት የማቅረብ ስልጣን አለው።
መንግሥት ምክረ-ሐሳቦቹን ተግባራዊ ካላደረገ ወይም ካዘገየ፣ ኮሚሽኑ ይኸው ተፈጻሚ እንዳልሆነ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት የማቅረብና አስገዳጅ እርምጃ እንዲወሰድ የመጠየቅ መብት አለው።

የመጨረሻ የምክክሩ ውጤቶች "በራሳቸው ጊዜ አስገዳጅ ሕግ" አይደሉም። ነገር ግን በአዋጁ መሠረት መንግሥት ምክረ-ሐሳቦቹን ተቀብሎ ወደ ተግባር፣ ወደ ሕግና ወደ ፖሊሲ የመቀየር የአሠራርና የሕግ ግዴታ (Procedural Bindingness) አለበት። የመጨረሻው ውጤት ስኬታማ የሚሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክትትል ጥንካሬና በመንግሥት ቁርጠኝነት ላይ መሠረት ያደረገ መሆኑን ከአዋጁ መረዳት የሚቻል ነው።

4. የጹሁፉ ማጠቃለያ

ይህ የምክክር ኮምሽኑ ከአስፈጻሚ አካላት ገለልተኛ ሆኖ በአዋጅ የተቋቋመ ሲሆን ሀገራዊ ምክረ ሀሳቦችን ላይ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ከሀገር ሰላምና ደህንነት ፣ እድገት እንጻር
አስፈላጊውን በማድረግ ለምክር ቤት አቅርቦ ተቀባይነት ካገኘ በመንግስት ወይም በአስፈጻሚ አካል ሊፈጸም የሚችል ሲሆን አፈጻጸሙን ምክር ቤቱ በዋናነት የሚከታተለው ሲሆን አፈጻጸሙ ላይ ጉድለት ከታየ ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በማቅረብ ተፈጻሚ እንዲሆን ሪፖርት የማድረግ ስልጣን አለው።

ማጠቃሻ/References/
1. የኢፊድሪ ህገመንግስት
2. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 1265/2014/

በፋንታሁን ደለለው
Fantahun Delelew, Lawyer
0929101037

delelewfantahun2010gmail.com
https://www.facebook.com/s...

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.