የቀጣናው ሀገራት የልማትና የትብብር ጸር - ፅምዶ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገወጡ የህወሓት ቡድን ከሻዕቢያና ከፅንፈኛ ቡድኖች ጋር በመሆን የፈጠሩት "ፅምዶ" የተሰኘ የጥፋት ቡድን ለትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ፤ እንዲሁም ለቀጣናው ሀገራት ተባብሮ የማደግ ጉዞ ጸር ነው፡፡
ህገወጡ ቡድን የጥቂት ግለሰቦችንና የግብፅን አጀንዳ የሚያስፈፅም የጸረ ሕዝብ ስብስብ ሲሆን፥ የሕዝብን የጭቆና ቀንበር ማራዘሚያ ነው፡፡
ህገወጡ ህወሓትና ሻዕቢያ በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ዓመታት ለሕዝብ ቃል የገቡትን ነጻነትም ይሁን ልማት ከማምጣት ይልቅ፤ ስልጣናቸውን ሲያደላድሉና ሀብት ሲዘርፉ ቆይተዋል፡፡
ይህ ስብስብ በኤርትራም ይሁን በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ሕዝባዊ ድጋፍና መሠረት የሌለው የግብፅ ተላላኪ ነው፡፡
የኤርትራ ሕዝብ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ያነሳቸው የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ዛሬም ሰሚ በማጣታቸው በሕዝቡ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር የተጣበቀውን አምባገነን ስርዓት ለመገርሰስ እየታገለ ይገኛል፡፡
በዚህ መንፈስ የተመሰረተው ግንባር ሕዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሃመዱ ከሰሞኑ በሰጠው መግለጫ፥ የኤርትራ ሕዝብ የጦርነት አባዜ የተጠናወተውን ጽምዶን እንደማይደግፍና ሴራውን ለማክሸፍ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡
በተመሳሳይ የትግራይ ሕዝብ ህገወጡን የህወሓት ቡድን የጦርነት ጉሰማ በጽኑ እየተቃወመ መሆኑን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
ህገወጥ ቡድኑ ከሕዝብ ለተነሳበት ተቃውሞ የሰጠው ምላሽ ተከታታይ አፋኝ አዋጆችን ማውጣትና የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ ማካሄድ ነው፡፡
ለሕዝብ ጥቅም ቆሜያለሁ የሚለው ይህ ቆሞ ቀር ቡድን የሕዝብን ሰብዓዊ መብቶች የሚጥሱ አፋኝና ጨቋኝ አዋጆችን በማውጣት ትክክለኛ ማንነቱን አሳይቷል፡፡
የግዳጅ የእህልና የገንዘብ መዋጮ በሕዝብ ላይ ከመጣል ባሻገር ወጣቶች ጦርነት በመሸሽ ከትግራይ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይሄዱ፤ እንዲሁም በጦርነት ዝግጅቱ ላይ ተቃውሞ እንዳይነሳ ከልክሏል፡፡
ይህ ሁሉ ድርጊት ህገወጡ ቡድኑ ጸረ ሕዝብ እና ጸረ ሰላም መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ተግባር ነው፡፡
ፅምዶ፤ ለግብፅ የሚላላኩት ሻዕቢያ፣ ህወሓትና ሌሎች ፅንፈኛ ቡድኖች የትግራይን ብሎም የኤርትራን ሕዝብ ስቃይና መከራ ለማራዘምና ቀጣናውን ለማተራመስ የተፈጠረ የጥፋት ስብስብ ነው፡፡
በአሁን ወቅት የኤርትራም ይሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልጉት ሰላምና ልማት እንጂ ጦርነትና ግጭት አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን ታሪኳ የገጠሟትን የውጭ ወረራዎችም ሆነ የውስጥ ባንዳዎች ሴራ በቆራጥ ልጆቿ ክንድ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የኖረችና የምትኖር ታላቅ ሀገር ናት።
በመሆኑም ኢትዮጵያ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የውጭ ጠላቶችንም ሆነ የውስጥ ባንዳዎችን ሴራ እያከሸፈች የልማት ግስጋሴዋን ትቀጥላለች።
በቴዎድሮስ ሳህለ

2 months ago