ሳይታጠብ እስከ አንድ ወር የሚቆይ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ቀረበ
አሜሪካዊው የልብስ ኩባንያ ‘ሄርክሊዮን’ ያለ ምንም እጥበት እስከ አንድ ወር ድረስ መጥፎ ጠረን ሳይይዝ በየቀኑ መልበስ የሚያስችል "HercShirt V5.0" የተሰኘ አዲስ ቲ-ሸርት ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።
ኩባንያው ለዚህ ፈጠራው መዳብ፣ ብር፣ ዚንክ፣ ወርቅ እና የእሳተ ገሞራ አመድን ጨምሮ ሰባት ልዩ ንጥረ ነገሮችን በጨርቁ ክር ውስጥ ማካተቱ ተገልጿል ።
እነዚህ ንጥረ ነገሮች ባክቴሪያዎችን ያግዳሉ፤ እርጥበትንም በመምጠጥ ልብሱ ምንጊዜም ይዘቱን ጠብቆ እንዲቆይ ያደርጋሉ ተብሏል።
አልፎ አልፎ ብቻ ስለሚታጠብ ከሰባት መደበኛ ቲ-ሸርቶች በላይ ያገለግላል የተባለው ይህ ምርት በ79 ዶላር ይሸጣል።
በተጨማሪም አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ ደንበኞች ለሶስት ቀናት የሚቆይ የ39 ዶላር አማራጭ እና እስከ ሁለት ሳምንት የሚያገለግል መደበኛ ስሪት መዘጋጀቱ ተጠቅሷል።
በቅርቡ በጥቁር ቀለም ሽያጩ የሚጀምረው ይህ ቲ-ሸርት፣ ወደፊት በሌሎች ቀለሞችም ለገበያ ይቀርባል መባሉ ተዘግቧል።
Seledadotio

4 hours ago