Logo
Getu Temesgen

በአንድ ዓመት ውስጥ ከመሠረት እስከ ጉልላት የደረሰው የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ድጋፍ ተጠየቀ

ብዙ ጊዜ በየሚዲያው የምንሰማው የችግርና የቅሬታ ዜና ቢሆንም፣ ዛሬ የምናካፍላችሁ የደስታና የተስፋ ዜና ነው።

በአዲስ አበባ የካ አባዶ ደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን የተመለከትነው ግንባታ እጅግ አስደናቂ የሚባል ነው።

ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር የመሠረት ሥራ ብቻ የነበረው ይህ ግዙፍ ቤተ ክርስቲያን፣ በአንድ ዓመት ውስጥ የግንባታው ሥራ እስከ ጣሪያና ጉልላት ደርሶ መታየቱ በርካቶችን አስደንቋል።

በዚህ ዘመን ብዙ አሳዛኝ ክስተቶች በሚሰሙበት ጊዜ፣ በትጋት የሚሠራ የግንባታ ኮሚቴ፣ ሰበካ ጉባኤ እና በልግስና የሚያግዙ ምዕመናን መኖራቸው የሚያበረታታ ተግባር ነው።

የቤተ ክርስቲያኑን ግንባታ ለማጠናቀቅ አሁን የሚፈለገው ድጋፍ የፊኒሺንግ ሥራዎችን፣ በሮችና መስኮቶችን፣ አንድ መንበር (ከአራቱ መንበሮች ሦስቱ በአካባቢው ምዕመናን ተይዘዋል)፣ ምንጣፍ፣ ቅዱሳት ሥዕላት፣ የኤሌክትሪክ ሥራዎች፣ ብሎኬት፣ ጂፕሰም፣ ቀለም ሥራዎችና ንዋየ ቅድሳትን ያካትታል።

ለዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ሥርጭት መርሐ ግብር በፊታችን ነሐሴ 1፣ 2 እና 5 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ይካሄዳል።

ድጋፍ ለማድረግ፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000635044482

ስልክ፦
0911426464

በቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ላይ በመሳተፍ የታሪክ ሠሪ ትውልድ አካል እንሁን።

አድራሻ፦
የካ አባዶ መሰቀለኛው ጋር ሲደርሱ ቁልቁል ወደ ግራ በሚወስደው መንገድ መጨረሻ።
6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.