Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ቡድን በሰላም ኦሪገን ደርሷል
#ethiopia | በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3፣ 2018 ዓ.ም በሚካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (World Athletics U20 Championships) የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ የተጓዘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን በሰላም ኦሪገን ደርሷል።

ሻምፒዮናው በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ልዩ ስፍራ ባለው የሄይዋርድ ፊልድ (Hayward Field) ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን፣ ይህ ስታዲየም በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮችንና ታሪካዊ የአትሌቲክስ ፉክክሮችን በማስተናገድ የታወቀ ነው።

በዘንድሮው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር (በሁለቱም ፆታዎች)፣ 3000 ሜትር መሰናክል (በሴቶች)፣ 400 ሜትር (በሴቶች) እና በርምጃ ውድድር (በሁለቱም ፆታዎች) በመሳተፍ ጠንካራ ውጤት ለማስመዝገብ በተጠናከረ ዝግጅት ቀርባለች።

ይህ ውድድር ለወጣት አትሌቶች ዓለም አቀፍ ልምድ የሚያስገኝ እና የወደፊት የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮኖች የሚፈጠሩበት አንዱ ትልቅ መድረክ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ቡድንም የሀገሪቱን የረጅም ርቀት አትሌቲክስ ስኬት ለማስቀጠል ተስፋ ተጥሎበታል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለመላው ልዑክ ቡድን የተሳካ ውድድርና የድል ጉዞ በመመኘት መልካም ዕድል ብሏል።

መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ቡድን! 🇪🇹

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

10 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.