Logo
EBC
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጋምቤላ ወደ ደምቢዶሎ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር ነው
********************

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹን በማስፋት ከጋምቤላ ደምቢዶሎ እና ከደምቢዶሎ ጋምቤላ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ይህን የበረራ አገልግሎት ከነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎቹን አቅም በየጊዜው በማስፋት የህብረተሰቡን የእንቅስቃሴና የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በጋምቤላ እና በደምቢዶሎ ከተሞች መካከል የሚጀመረው ይህ አዲስ የበረራ መስመር፣ በሁለቱ አካባቢዎች መካከል ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከርና ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አየር መንገዱ ለኢቢሲ ዶትስትሪም በሰጠው መረጃ አስታውቋል።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.