Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱማሊያው ፕሬዝደንት ‹‹ቀይ ባህርን እያተራመሰች ያለችው እስራኤል ናት›› አሉ፡፡ የሱማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ትላንት የፌዴራል መንግስቱ ፓርላማ ስምንተኛ ጉባኤ የመክፈቻ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር እስራኤል በአገራቸው ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እስራኤል እያደረገች ያለው ይህ ጣልቃ ገብነት የአገራቸውን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት የሚጥስ መሆኑን ጠቁመው ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹እስራኤል በሱማሊያ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ እያደረገች ያለው ጣልቃ ገብነት በአፍሪካ ቀንድና ቀይ ባህር አካባቢ ላይ አለመረጋጋትና ትርምስ እንዲፈጠር ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡›› ያሉት ፕሬዝደንቱ የአገራቸውን ሉአላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት መከላከላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

ሱማሊያ ያጋጠማችን የፖለቲካና የፀጥታ ፈተናዎች ለመጋፈጥ የመንግስት ተቋማትን ማጠናከርና አስተዳደርን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ያሳሰቡት ፕሬዝደንቱ ብሄራዊ ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረትም መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ በንግግራቸው በአስራኤል ላይ ጠንካራ ትችት የሰነዘሩት እስራኤል ሱማሊያ ‹‹ግዛቴ ናት›› ለምትለው ሱማሊላንድ እውቅና በመስጠቷ ነው፡፡

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.