Logo
SeledaPost
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲዘዋወሩ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ።

በትግራይ በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተወሰኑ ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

በመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ጥያቄያቸውን ለመንግሥት እያቀረቡ ነው።

ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ በሚታየው የጸጥታ ስጋት ምክንያት የቅሬታ ጥያቄ እያስገቡ ሲሆን፤ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ የዝውውር ውሳኔም ሆነ የተገባ ቃል አለመኖሩን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሓየሎም ስዩም ገልፀዋል።

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.