(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፖለቲካ ትንታኔ አቅራቢው ሬኔ ሌፎርት በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ተቀሰቀሰ ስለተባለው ትጥቃዊ ግጭት የሚወጡ ዘገባዎችን ለመተንተን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ተንታኙ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ ለዚህ ጥንቃቄ በምክንያትነት ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የፌደራል መንግስቱ (አዲስ አበባ) ሙሉ በሙሉ ዝምታን መምረጡ እና የህወሓት መረጃዎች ተዓማኒነት አጠያያቂ መሆኑ ይገኙበታል።
አያይዘውም ውጊያው እንደተዘገበው በሸረሪና አካባቢ የጀመረ ከሆነ፣ በግጭቱ የተሳተፉት ኃይሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት (ENDF)፣ አዲስ አበባን የሚደግፉ የአማራ ሚሊሻዎች እና አጠቃላይ የትግራይ መከላከያ ኃይልን (TDF) ሳያካትት የትግራይ ሰራዊት 'አርሚ 70' ኮር ብቻ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመላክተዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በውጊያው ውስጥ በትክክል ስለመሳተፉ እስካሁን የታወቀ ነገር እንደሌለ እና ግልጽ ያልሆነ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ሬኔ ሌፎርት አሁን ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ሁለት ሊሆኑ የሚችሉ ግምቶችን አስቀምጠዋል። የመጀመሪያው፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግጭቱን ለመከላከል ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ቢሆንም፣ ይህ ክስተት በመላው የአፍሪካ ቀንድ ሊስፋፋ የሚችል አውዳሚ ጦርነት መነሻ ሊሆን እንደሚችል ነው።
ሁለተኛው ግምት ደግሞ "ያዙኝ ካለበለዚያ ጥፋት አደርሳለሁ" በሚል ስሌት፣ ሸምጋዮችን በማስገደድ የተፈጠረውን የፖለቲካ ማነቆ በድርድር ለመፍታት የተተኮሰ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ሊሆን እንደሚችል ነው። ሆኖም ክስተቱ ከሁለቱ የትኛው እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመናገር አሁንም በጣም ገና መሆኑን ትንታኔያቸው ያሳያል።

3 days ago