(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቻይናው ዚጂን ማይኒንግ (የካናዳውን አላይድ ጎልድን በ4.01 ቢሊዮን ዶላር (5.5 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር) ለመግዛት ያደረገው ስምምነት በቻይና እና በኢትዮጵያ መንግስታት ጫና ምክንያት መፍረሱ ተገለጸ።
እ.ኤ.አ. በጥር 2026 የተደረሰው ይህ ስምምነት፣ ዚጂን ማይኒንግ በአላይድ ጎልድ ስር የሚገኙትንና በኮትዲቯር፣ ማሊ እና ኢትዮጵያ (ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚገኘው የኩርሙክ የወርቅ ማዕድን) ያሉትን ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ እንዲገዛ የሚያስችል ነበር። ስምምነቱን የካናዳ እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተቋማት (እንደ ኮሜሳ እና ኤኮዋስ) ቢያጸድቁትም፣ የቻይና ብሔራዊ ልማት እና ማሻሻያ ኮሚሽን (NDRC) የግዢውን ዋጋ እና የማሊን የፖለቲካ አለመረጋጋት በመስጋት ማጽደቅ አልቻለም።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት በዚሁ ስምምነት ዙሪያ ከፍተኛ የግብር ጥያቄዎችን ማንሳቱ ለድርድሩ መፍረስ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። የኢትዮጵያ ገቢዎች ህግ የውጭ ኩባንያዎች የባለቤትነት ለውጥ ሲያደርጉ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ ያስገድዳል። በተጨማሪም፣ የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ኩርሙክ ያለን ስትራቴጂካዊ የወርቅ ማዕድን በአንድ የቻይና የመንግስት ኩባንያ ስር ብቻ እንዲወድቅ አለመፈለጉ ሌላው ተግዳሮት ነበር።
በእነዚህ ጂኦፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ እንቅፋቶች ምክንያት ሁለቱ ኩባንያዎች ሙሉ ግዥውን ሰርዘዋል። በምትኩ፣ ዚጂን ማይኒንግ 295 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል 9.2 በመቶ የአላይድ ጎልድ አክሲዮኖችን (Strategic Equity Stake) ብቻ ለመግዛት ተስማምቷል። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላ በቶሮንቶ እና ኒውዮርክ የአክሲዮን ገበያዎች ላይ የአላይድ ጎልድ የአክሲዮን ዋጋ ከ16 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል።

5 days ago