(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከኢራን ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት የወጣው አዲስ ማስጠንቀቂያ በቀጠናው ያለውን ወታደራዊ ፍጥጫ ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
ቴህራን ባወጣችው መግለጫ፣ አሜሪካ በደቡባዊ የኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን የባህር ኃይል እገዳ የምትቀጥል ከሆነ፣ በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ ያለው ቁጥጥር ይበልጥ እንደሚጠበቅና ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች የባህር መተላለፊያ ሰርጦች ሊዘጉ ወይም ሊቆለፉ እንደሚችሉ ዝታለች።
ኢራን በመግለጫዋ ላይ የሌሎቹን የባህር ሰርጦች ስም በግልጽ ባትጠቅስም፣ ከቴህራን ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው ሁቲዎች የሚቆጣጠሩት የባቢል መንደብ የባህር ሰርጥ እና የኤደን ባህረ ሰላጤ መሆናቸውን በቀላሉ መረዳት ይቻላል።
የኢራን መንግስት አሜሪካ እገዳውን የምትገፋበት ከሆነ የዓለም አቀፉ የኃይል (የነዳጅ) ገበያ ክፉኛ እንደሚናወጥ አስታውቋል። መግለጫው የአሜሪካ መራጮችንም ጭምር ያነጣጠረ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም መስተጓጎል በአሜሪካ የአገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታወቀ ነው።
በዚህም አኳኋን ቴህራን አዲስ የመደራደሪያ እና የማስፈራሪያ እኩልዮሽ በመዘርጋት፣ ለአሜሪካ ማንኛውም እርምጃ የኃይል ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀች ይመስላል።
ይህ የኢራን ማስፈራሪያ የመጣው፣ አሜሪካ እና እስራኤል የኢራንን የኃይል እና የነዳጅ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ ሊከፍቱ ይችላሉ የሚሉ ግምቶች በበረቱበት ወቅት መሆኑ ዘገባውን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል።

4 days ago