(ዘ-ሐበሻ ዜና) [የሰኔ 16ቱ ጉዳይ] የፖለቲካ ሴራ ተንታኞች መጠቀምያም ሆኗል። ታስታውስ ከሆነ እለቱ ቅዳሜ ነበር፣ ዊኬንድ ነበር፣ ማምሻ ላይ ነበር ይሄ ጉዳይ የተፈጠረው። እና እኔ እዚህ ቢሮ ቆይቼ ከቢሮ ስወጣ ነው መረጃው የሰማሁት። እና ለሚዲያ መነገር አለበት የሚል ሀሳብ መጥቶ የሚዲያ አካላት ይጠሩ ብለን ፋና፣ ኢቢሲ፣ አሚኮ ተጠርተው ነበር። መግለጫ የሰጠሁበትን ቦታ እስከዛሬ አስታውሰዋለሁ እኔ። ነገር ግን ፋና እና ኢቢሲ ምናልባትም ዊኬንድ ስለሆነ ምሽትም ስለነበረ ስንጠራቸው በዚያ ፍጥነት አልመጡልንም፣ አሚኮ ግን ጎረቤት ነው እዚህ 4 ኪሎ ነው መስሪያ ቤቱ፣ መኪናም ላያስፈልገው ይችላል - እዚሁ ስለሆነ። ልክ ጥሪው ሲደረግ ወዲያው አሚኮ መጣ፣ አሚኮ መጥቶ የተወሰነ ደቂቃ ጠበቀን እነዚያ ቢደርሱ ብለን፣ ዘገዩብን። እና መጨረሻ የመጣው ሀሳብ 'ምንም እኮ ችግር የለውም አሚኮ ወስዶ ለሁሉም ሊያከፋፍል ስለሚችል ለአሚኮ ይሰጥ ተብሎ እኔ ቤት ነው ለአሚኮ የሰጠሁት። በኋላ ግን ባህርዳር ላይ ሆኖ መግለጫ የሰጠው ወደሚል የሴራ ትንተና ተቀይሯል። እንደዚህ ያለው ከእውነት የተፋታ፣ ዛሬም ለነገም የማይበጅ፣ ውስጥህ እያወቀ የሚሸነገል፣ የሚዋሽ ነገር ጥፋት ብቻ ነው የሚያመጣው እና... ያ ክስተት ከመነሻው የሚሳካ ነው፣ ከመነሻው አንድ ግብ የሚያሟላ ነው ባትልም፣ እንደ ጥቁር ጠባሳ የሚወሰድ መጥፎ ክስተት ነው ብዬ ነው የማየው።"
ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አህመድ
4 days ago