Logo
SeledaPost
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለት የሚዲያ ተቋማት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚዲያ ተቋማት ሕግና የሙያ ሥነ ምግባርን አክብረው መስራታቸውን እየተከታተለ ድጋፍና እርምት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት፦
• አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና
• አርትስ ቴሌቪዥን
የተሰጣቸውን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ፣ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሬድዮ እና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር በተስተዋሉ ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ጥሰቶች ላይ ውይይቶች ያደረገ ቢሆንም ጉልህ ለውጥ ሳይታይ በመቅረቱ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያስታውቃል፡፡

ስለሆነም ጣቢያዎቹ በቀጣይ ሥራቸውን በሕግና በሙያ ሥነ ምግባር መሠረት እንዲያከናውኑ በጥብቅ ለማሳሰብ ይወዳል።

ባለስልጣኑ ማስጠንቀቂያው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 74/ሠ መሠረት የተሰጠ መሆኑን እየገለፀ ሚዲያዎቹ ተመሳሳይ የህግ መተላለፍ እና ጥሰት እየፈፀሙ የሚቀጥሉ ከሆነ በህጉ መሠረት ቀጣይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ባለሥልጣኑ ያስታውቃል።

ባለስልጣኑ የሚዲያ ተቋማት በሁሉም የዘገባ ስራዎቻቸው ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና የሀገሪቱን ሕጎች እንዲሁም የዘርፉን የሙያ ሥነ ምግባር አክብሮ መስራት የሁሉም ግዴታ መሆኑን  ለአፍታም ሊዘነጉት እንደማይገባ ያሳስባል።

Seledadotio
Seledadotio
6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.