ለሀገር ዕድገትና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት የጸና አገራዊ ቁርጠኝነት!
ኩባንያችን የኢትዮጵያን የዲጂታልና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በግንባር ቀደምትነት እየመራ፣ ለሀገር ግንባታና ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያደርገውን የማይተካ አገራዊ አስተዋፅኦ በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 73.5 ቢሊዮን ብር ታክስ ገቢ በማድረግ የሀገር ግንባታ ምሰሶነቱን ያስመሰከረ ሲሆን፣ ይህም ተቋማችን ያስገባቸውን አጠቃላይ የታክስ መጠን 244.5 ቢሊዮን ብር አድርሶታል። ከዚህ ቀደምም ኩባንያችን ለተከታታይ 5 ዓመታት የሀገሪቱ ግንባር ቀደም የፕላቲኒየም ግብር ከፋይና ልዩ ሽልማት ባለቤት መሆኑ ይታወሳል።
ከታማኝ ግብር ከፋይነቱ በተጨማሪ፣ ተቋማችን ከውድ ደንበኞቹ ጋር በመተባበር 2.4 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊ አደጋ ማገገሚያ ፈንድ በማሰባሰብ፣ በችግር ጊዜ ለወገን አለኝታነቱን በተግባር ዳግመኛ አስመስክሯል። ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እየተወጣ የሚገኘው ኩባንያችን፣ ለ44,757 ዜጎች ቀጥተኛ የቋሚና የውል ሥራ ዕድል በመፍጠር የበርካታ ቤተሰቦችን ኑሮ መደገፍ ችሏል።
በተጨማሪም ኩባንያችን 519,810 የምርትና አገልግሎት አከፋፋዮችንና የቴሌብር ወኪሎችን፣ 2,205 የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችን፣ 1,213 የተጨማሪ እሴት አገልግሎት አጋሮችን፣ 138 የፍራንቻይዝ አጋሮችንና 693 ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማቀፍ ከ2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ የሚፈጥር ግዙፍ የኢኮኖሚ ሥነ-ምህዳር መገንባት ችሏል።
በቀጣይም ኩባንያችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጠራን ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጋር በማቀናጀት፣ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ የማፋጠን፣ የሥራ ዕድል የመፍጠርና የታማኝ ግብር ከፋይነት አገራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ መወጣቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ለበለጠ፡ https://bit.ly/45k6Gjw
#ethiotelecom

8 days ago