Logo
SeledaPost
ከቁሉቢ ገብርኤል ንግስ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የነበሩ ሁለት የአንድ ቤተሰብ አባላት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ

​በኦሮሚያ ክልል አለልቱ አካባቢ በደረሰ አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ ከቁሉቢ ገብርኤል ንግስ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የነበሩ ሁለት የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉ ተሰምቷል። የአሌልቱ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር መርድ ሙሉጌታ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ሐምሌ 21ቀን 2018 ከቀኑ ስምንት ሰዓት አደጋው ደርሷል።

በሠሜን ሸዋ ዞን አለሊቱ ወረዳ  ጮሌ ቀበሌ ውስጥ፣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A-27185 ኢቲ
​ ጠጠር የጫነ ሲኖትራክ ከባድ ተሽከርካሪ ሌላ ተሽከርካሪ በመደረብ ለማለፍ ሲሞክር፣ ከሚኒባስ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው ደርሷል።

​በሚኒባስ ተሽከርካሪው ውስጥ ይጓዙ የነበሩት የደብረ ብርሐን ከተማ አጂፕ አካባቢ ነዋሪዎችና የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ፣ የቁሉቢ ገብርኤል ንግስ አንግሠው ወደ  ቤታቸው ሲጓዙ አደጋው እንዳጋጠማቸው ገልፀዋል።በዚሁ አደጋ  ወዲያው ሑለት ሴቶች ሲሞቱ ፣በሚኒባሱ ሹፌር ና ሁለት ህፃናት ላይ  ከባድ ጉዳት በሌሎች አራት ሠዎች ላይ ደግሞ ቀላል አደጋ ስለደረሰበቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ።

በአንዳንድ የማሕበራዊ ሚዲያ የሟቾች ቁጥር አራት ተብሎ ቢገለፅም እስካሑን ድረስ የደረሣቸው መረጃ እንደሌለ ኢንስፔክተር  መርድ ሙሉጌታ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Seledadotio
Seledadotio
7 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.