Logo
Zehabesha
"አቶ ቢኒያም ሙሰማ ሀሽም የ(ELMIS) ፕሮጀክት ኦፕሬሽን ማናጀር ሲሆኑ ከአቶ ብርሃኑ አለቃ ጋር በመሆን የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኦንላይን (online) ሲስተሙ እንዳይሰራ በማድረግ ከኤጀንሲዎች እና ከግለሰቦች ጋር በገንዘብ በመደራደር ሲስተም እንዲሰራላቸው በማድረግ፤ ያለምንም ጥፋት የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን በማገድ እና በማሰር በገንዘብ በመደራደር እንዲለቀቁ እና እግዱ እንዲነሳላቸው ያደርጋል፤ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ዜጎች የብቃት ምዘና ፈተና (COC) ሳይፈተኑ እና ተገቢውን ስልጠና ሳይወስዱ እንዳለፉ በማስመሰል ሀሰተኛ ዶክመንት በመስጠት ከኤጀንሲዎች ጋር በመደራደር ሀገር ውስጥ ማስገባት የሚገባቸውን ኮሚሽን ሳያስገቡ እንዳስገቡ በማስመሰል ለኤጀንሲዎች ሀሰተኛ የኮሚሽን ሪፖርት በማዘጋጀት ሀገሪቱ ማግኘት ያለባትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ አሳጥቷል፤ በዚህ ህገ-ወጥ ተግባርም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከፈተው ሁለት ሂሳብ ቁጥር 16,599,554 (አስራ ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ አምሳ አራት) ብር ገቢ ተደርጎለታል፡፡"

የፌዴራል ፖሊስ በሥራ እና ክህሎት ሚ/ር ባለስልጣናት ላይ ከመሰረተው ክስ መዝገብ ላይ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.