Logo
Getu Temesgen
1.69 ትሪሊዮን ብር : አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ
እንኳን ደስ አለን!! እንኳን ደስ አላችሁ!!
#ethiopia | ባጠናቀቅነው በጀት ዓመት ብቻ ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ አሰባስበን አጠቃላይ ተቀማጭ 1.69 ትሪሊዮን ብር በማድረስ ታላቅ ስኬት አስመዝግበናል

የተከበራችሁ ደምበኞቻችንና የተወደዳችሁ የባንካችን ሰራተኞች!፤
ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ፤
ባጠናቀቅነው የ2024/25 በጀት ዓመት በፈረንጆቹ ጁን ወር መጨረሻ፤ ባንካችን ከ515 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባር በማሳካቱ የተሰማኝን ከፍ ያለ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በባንካችን የተመዘገበ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ለዚሁ ታላቅ ስኬት አሻራችሁን ላኖራችሁ ሁሉ እንኳን ደሰ አላችሁ እላለሁ፡፡
በተለይም ባንካችን ላይ እምነታችሁን አሳድራችሁ አብራችሁን ለሰራችሁ ውድ ደንበኞቻችን ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ይህ ስኬት የናንተ እገዛና ያላሰለሰ ጥረት ድምር ውጤት ነው፡፡ የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አመራሮችና አባላት ለውጤቱ መሳካት ያደረጋችሁት ክትትልና ድጋፍ የነበረው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው፡፡ ድካማችሁ ፍሬ አፍርቶ ለማየት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የባንካችን የስራ አመራር አባላት፣ የሪጅን እና የዋናው መ/ቤት ሰራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክቶችና የቅርንጫፍ ሰራተኞቻችን፣ የባንካችንን ስትራቴጂዎች እና አቅጣጫዎች ለመተግበር ያሳያችሁት ቁርጠኝነት ለስኬቱ ከፍ ያለ ሚና አበርክቷል፡፡
እዚህ ስኬት ላይ ለመድረስ ያሳየነው ታታሪነት እና ትጋት ፍሬ ሰጥቶን ለማየት በመብቃታችን ስሜቱ ጥልቅ ነው፡፡ በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎቻችን በትብብርና በትጋት የመስራት ውጤት አስረጅ ነው፡፡ የባንካችን ሰራተኞች በጋራ ሆነን እና ተናበን ያሳየነው ጥረት ውጤት ለመሆኑም ጥርጥር የለውም፡፡
ደንበኞቻችንን ለማገልገል ባሳየነው ቁርጠኝነት የተገኘ የላቀ አፈጻጸም ስለመሆኑም አምናለሁ፡፡ ደንበኞቻችንን በማስቀደም እና ፍላጎታቸውን በመረዳት፤ ተገቢውን አገልግሎት ለማቅረብ ያደረግነው ትጋት ማሳያ ነው፡፡

ለባንካችን ይህ ስኬት ትርጉሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህም፡-
 የባንካችን ሰራተኞች ታታሪነትና ጠንካራነት ማሳያ
 በትብብር የመስራት እና ለአንድ ዓላማ የመቆም ምልክት
 ለባንካችን ያለንን ፍቅርና የባለቤትነት ስሜት ምስክር
 ለደንበኞቻችን የምንሰጠውን አክብሮትና ዋጋ የገለጽንበት እና
 የባንካችንን ራዕይ ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት ያመላከትንበት ነው ማለትም ይቻላል፡፡

በሌላ መልኩም ባንካችን ፈተናዎችን እና ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ በጥንካሬ እና በከፍታ መዝለቅ የቻለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
የተከበራችሁ የባንካችን ሰራተኞች!፤
ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ለነበራችሁ ትጋት ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ያሳየነው ስኬት ድንቅ እና ሁላችንንም የሚያስደምም ነው፡፡ ሁላችንም ልንኮራ ይገባናል። ለመጪው በጀት ዓመት ታላቅ ስንቅ ሆኖን በላቀ ከፍታ ለመጓዝ ጠንክረን እንቀጥል፡፡

ለተሻለ ስኬት እንትጋ!
አመሰግናለሁ፡፡

አቤ ሳኖ
ፕሬዝዳንት

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.