"የተሰደድኩበትን ቂም ትቼ ልመካከር መጥቻለሁ" - ፓስተር ፖች ኦኩዌር
******************
ከ22 ዓመታት በፊት በጋምቤላ በደረሰው አሳዛኝ ግጭት አባታቸውን፣ አጎታቸውንና የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን በአንድ ቀን ያጡት ፓስተር ፖች ኦኮዌር፤ ለዓመታት የዘለቀውን የልብ ስቃይና ቁስል በበቀል ሳይሆን በይቅርታ ለመፈወስ የወሰኑበትን ታሪክ ያካፍላሉ።
ያ ከባድ ሀዘን እና ቁርሾ ውስጣቸውን ለዘመናት ሲያንገበግበው ቢኖርም፤ "ያኔ ብንመክር ይህ አይፈጠርም ነበር፤ ዛሬ መክረን መጠፋፋት በእኛ ይብቃ ልንል ይገባል" በማለት ቂማቸውን ወደ ይቅርታ በመቀየር በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከአውስትራሊያ በመምጣት በዚሁ ታሪካዊ የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት ፓስተር ፖች፣ ሀገራዊ መግባባት የሚጀምረው ከግል ይቅርታ እንደሆነ ይመሰክራሉ።
ፓስተር ፖች፤ ላለፉት በርካታ ዘመናት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከማቹ በርካታ ቁስሎችና አለመግባባቶች ዋናው ምክንያት አለመነጋገርና አለመመካከር መሆኑን ይናገራሉ።
ሰዎች በግልጽ በሚነጋገሩበት ወቅት አንዱ የሌላውን ሕመም የመረዳት አቅም ያገኛል፤ ይህ ደግሞ በቂም የተዘጉ በሮችን በመክፈት የጠፉ ፍቅሮችንና የቤተሰባዊነት ስሜትን ይመልሳል ይላሉ።
የቤተሰብ አባልን በግፍ ማጣት ከፍተኛ የልብ ስቃይ የሚያስከትል ቢሆንም፣ በበቀል ስሜት የሚወሰድ እርምጃ ግን ጥፋቱን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍ ተጨማሪ ቁስል ከመፍጠር እንደማይዘል ፓስተር ፖች ይገልፃሉ።
ይቅርታ ማድረግ የደረሰውን በደል መካድ ሳይሆን፣ የበቀልን ከባድ ሸክም አውርዶ በማስቀመጥ ለተሻለና ለሰላማዊ ነገ መንገድ የመክፈት ጥበብ መሆኑንም ይናገራሉ።
ዛሬ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሰፊና አካታች መክክር ለሀገሪቱ ትንሣኤ ትልቅ ጅምር መሆኑን በመጥቀስ፤ በተለይም አዲሱ ትውልድ ከቂም፣ ከጥላቻና ከመገዳደል አዙሪት ወጥቶ በፍቅርና በመቻቻል እንዲኖር ትልቅ በር እንደሚከፍት ይገልጻሉ።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መድረክ መፈጠሩ ለነገዋ ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ እንደሆነም ይጠቁማሉ።
በእውነትና በይቅርታ ላይ የተመሰረተ ውይይት ሀገራችንን ወደ ተሻለች ከፍታ እንደሚያሸጋግራት ፓስተር ፖች ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልፀዋል።
#ebc #ethiopia #ethiopiannationaldialogue #nationalconsensus
ሙሉ ታሪኩን በአስተያየት መስጫው ላይ ያገኙታል፡-

2 months ago