(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ለጎብኚዎች፣ ለንግድ ሰዎች እና ለቤተሰብ ጥሪ አገልግሎት የሚውል ለአምስት ዓመታት የሚያገለግል የብዙ ጊዜ መግቢያ (5-year multiple entry visa) ቪዛ በማቅረብ የዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና የሥራ ማዕከልነቷን እያጠናከረች መሆኑን አስታወቀች። ይህ የቪዛ ዓይነት ማንኛውም የዓለም ዜጋ በየጊዜው አዲስ ቪዛ ማውጣት ሳያስፈልገው ለአምስት ዓመታት ያህል በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገባና እንዲወጣ የሚያስችል ነው።
በአንድ ጊዜ መግቢያ ላይ ጎብኚዎች ለአምስት ዓመታት የቪዛ ዘመን ውስጥ በዓመት እስከ 90 ቀናት ድረስ መቆየት የሚችሉ ሲሆን፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ይህን የቆይታ ጊዜ ለተጨማሪ 90 ቀናት በማራዘም በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ 180 ቀናት እንዲቆዩ ይፈቅዳል። ይህ አሰራር በዓመቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ቀናትን ወደሚቀጥለው ዓመት ለማዘዋወር አይፈቅድም።
የቪዛው አመልካቾች ማሟላት ከሚገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች መካከል ቢያንስ ለስድስት ወራት የሚያገለግል ፓስፖርት፣ የተረጋገጠ የጉዞ ትኬት፣ ሕጋዊ የጤና ኢንሹራንስ፣ እና ማመልከቻው ከመግባቱ በፊት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 4 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም ተመሳሳይ መጠን ያለው የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የቤተሰብ ማመልከቻ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን፣ የአንዳንድ አገራት ዜጎች ደግሞ የመታወቂያ ኮፒ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።
አመልካቾች በይነመረብን በመጠቀም በስማርት አገልግሎቶች ወይም በአካል ወደ ደንበኞች ማዕከል በመሄድ ማመልከት የሚችሉ ሲሆን፣ የቪዛ ሂደቱም በ48 ሰዓታት ውስጥ ይጠናቀቃል። የቪዛው ክፍያ እንደ ማመልከቻው ቦታ የሚለያይ ሲሆን፣ የዋስትና ገንዘብን (ዲፖዚት) ጨምሮ ከ3,700 በላይ ዲርሃም ወጪ ይደረግበታል። ማመልከቻው ውድቅ ከተደረገ ወይም ከተሰረዘ የተቀመጠው የዋስትና ገንዘብ እና የኢንሹራንስ ክፍያ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን፣ የቆይታ ጊዜ ሕግ ከተጣሰ ግን የተቀመጠው የዋስትና ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።

13 days ago