የቀድሞው የኤርትራ ትምህርት ሚኒስትርና በኢትዮጵያ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም በ83 ዓመታቸው አረፉ
#ethiopia | አስመራ – የቀድሞው የኤርትራ ትምህርት ሚኒስትርና በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሰመረ ርዕሶም በ83 ዓመታቸው በሕመም ምክንያት ማረፋቸውን የኤርትራ መንግሥት አስታውቋል።
አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም በ1976 የኤርትራ ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር (EPLF) በመቀላቀል የትግል ጉዞዋቸውን የጀመሩ ሲሆን፣ ከኤርትራ ነፃነት በኋላ በሱዳን የጊዜያዊ መንግሥት ዋና ጸሐፊ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር፣ በአሜሪካ የኤርትራ አምባሳደር፣ የማዕከላዊ ክልል አስተዳዳሪ፣ የአስመራ ከንቲባ እና ከ2007 ጀምሮ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
እ.ኤ.አ. በ2018 ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ20 ዓመታት በላይ ከቆየው የዲፕሎማሲ መቋረጥ በኋላ ግንኙነታቸውን ሲያድሱ፣ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም በአዲስ አበባ የኤርትራ የመጀመሪያ አምባሳደር ሆነው ተሾመው በሁለቱ ሀገራት መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲመለስ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
የኤርትራ መንግሥት አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል አገራቸውን በታማኝነት እንዳገለገሉ ገልጾ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በሐምሌ 24 በአስመራ የሰማዕታት መቃብር ስፍራ እንደሚፈጸም አስታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

13 days ago