Logo
YenetaTube
የኬንያ መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ በሙሉ በበጀት ሊሸፈን መሆኑን አስታወቀ

የኬንያ መንግስት ከሚቀጥለው መስከረም 2026 ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገቡ ሁሉንም ተማሪዎች ትምህርት ሙሉ በሙሉ በመንግስት በጀት እንደሚሸፈን ይፋ አደረገ። ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ አዲሱ የትምህርት ፋይናንስ ማዕቀፍ ከቤተሰብ ኢኮኖሚያዊ አቅም ውጪ በውጤት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ተግባራዊ ተደርገው የነበሩት የዩኒቨርሲቲ በጀት አሰጣጥ ሥርዓቶችና የብድር ድብልቅ ሞዴሎች ተቋማቱንና ተማሪዎችን በቂ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻላቸው መቋረጣቸውን ተናግረዋል።

አዲሱ ሥርዓት ወላጆች በፈቃደኝነት ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት የክፍያ ጫና እንዳይኖርባቸው የሚያደርግና ድህነት ትምህርት እንዳያስተጓጉል የሚያስችል ነው ተብሏል። ለዚህም እንዲመች ፓርላማው የከፍተኛ ትምህርት ብድር ቦርድን ጨምሮ አስፈላጊውን የህግ ማሻሻያ በፍጥነት እንዲያጸድቅ ተጠይቋል።

Via capital

15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.