Logo
YenetaTube
የህንድ ዋና ከተማ ዴሊ የትምህርት ሚኒስትሩ ስልጣን እንዲለቁ በሚጠይቁ ሰልፈኞች ተጥለቅልቃለች

በሺዎች የሚቆጠሩ ህንዳውያን ሰልፈኞች የፖሊስን እገዳ በመጣስ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር ከስልጣናቸው እንዲወርዱ በመጠየቅ በዋና ከተማዋ ዴሊ ግዙፍ ተቃውሞ እያካሄዱ እንደሚገኙ ዘ ጋርድያን ዘግቧል።

የሰልፉ ዋና ጥያቄ የህክምና ትምህርት መግቢያ ፈተና ተሰርቆ መሸጡን እና ፈተናው ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ መደረጉን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስትሩ ዳርሜንድራ ፕራዳን ከስልጣን እንዲለቁ ነው። ከ2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ለ130,000 ቦታዎች የሚፎካከሩበት ይህ ፈተና መሰረዙ ከፍተኛ ቀውስ የፈጠረ ሲሆን፣ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ከ20 በላይ ተማሪዎች ህይወታቸውን ማጥፋታቸው ተነግሯል።

ይህ ሰልፍ ህንድ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ካየቻቸው ትልልቅ መንግስታዊ ተቃውሞዎች አንዱ እንደሆነ ተገልጻል።በአብዛኛው በተማሪዎች እና በወጣቶች የተሞላው ሰልፉ ከሰኞ ማለዳ ጀምሮ በዴሊ እምብርት በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ በመሰብሰብ መንግስትን የሚቃወሙ መፈክሮችን ያሰማ ነበር።

በማዕከላዊው መንግስት ስር የሚተዳደረው የዴሊ ፖሊስ ለሰልፉ ፈቃድ ያልሰጠ ሲሆን፣ በማንኛውም ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ እገዳ ጥሎ፣ መንገዶችን ዘግቶ እንዲሁም በከተማዋ መሀል የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርጎ ነበር።

ሰልፈኞቹ ወደ ፓርላማው ህንፃ ለማቅናት ባደረጉት ሙከራ ከፖሊስ በኩል የድብደባ እና የአስለቃሽ ጢስ ጥቃት ገጥሟቸዋል።ሆኖም ተቃዋሚዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና ገዢው የባራቲያ ጃናታ ፓርቲ (BJP) የሀገሪቱን ወጣቶች ችላ ብለዋል ሲሉ በከፍተኛ ቁጣ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

ይህ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ የቀረበው "ኮክሮች ጃንታ ፓርቲ" (CJP) በተሰኘ ወጣት መሪዎች በተመሰረተ አዲስ እንቅስቃሴ ነው። የፓርቲው ስም የመጣው በግንቦት ወር የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ ሶሪያ ካንት አክቲቪስቶችን እና ስራ አጥ ወጣቶችን "በረሮዎች" ብለው ከሰደቧቸው በኋላ ነበር።

ሀናን ሸምሱ

17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.