Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያውያን ደግነት ህልሜን እውን አደረገው! — ተማሪ ልዑል ብሬነህ
#ethiopia | በዘንድሮው አገራዊ የኢትዮ ሮቦቲክስ ውድድር አሸናፊ ሆኜ፣ በካናዳ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ለመወከል ዕድል ባገኝም፣ ለጉዞው የሚያስፈልገውን ወጪ መሸፈን ለቤተሰቤ ትልቅ ፈተና ሆኖ ነበር።

ነገር ግን በ"ታዲያስ አዲስ" የሬዲዮ ፕሮግራም እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች አማካኝነት ያቀረብኩትን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ፣ በጎ ፈቃደኛና ሩኅሩኅ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለጉዞዬ የሚያስፈልገኝን የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ እንዲሟላ አድርጋችሁኛል።

ህልሜ እውን እንዲሆን ከጎኔ ለቆማችሁ ለሁሉም ለጋስ ኢትዮጵያውያን በራሴና በቤተሰቤ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በተለይም ድምፄ ለብዙኃን እንዲደርስ መድረኩን ያለምንም ክፍያ ለከፈተልኝ "ታዲያስ አዲስ" የሬዲዮ ፕሮግራም፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ስልጠና በመስጠት እና የካናዳ ጉዞዬን ሙሉ በሙሉ ላመቻቸለልኝ ኢትዮ ሮቦቲክስ ማዕከል፣ እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ላደረጉልኝ ወ/ሮ ኑርያ ከማል እና አቶ ፋሲል ሰለሞን ልዩ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁ።

በተጨማሪም መልዕክቴን ያለምንም ክፍያ በገጾቻችሁ በማጋራት ድጋፍ ላደረጋችሁ የማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች፣ እንዲሁም ከአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በገንዘብ፣ በሃሳብ እና በማበረታቻ ከጎኔ ለቆማችሁ ሁሉ ፈጣሪ የደግነታችሁን ዋጋ ይክፈላችሁ።

ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በክብር ለመወከል ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።

ከልብ አመሰግናለሁ!

– ተማሪ ልዑል ብሬነህ

19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.