Logo
SeledaPost
''አዳዲስ ቀረጦች ሊጣሉ ነው‼️
በነዳጅ፣ በሪል እስቴት፣ በአልኮልና በትምባሆ እንዲሁም በኢንቨስትመንት ታክስ ነፃ መብቶች ላይ አዳዲስ ቀረጦች ሊጣሉ መሆኑ ተሰምቷል።

IMF እንደገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት 5 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ብድር ለማግኘት ሲል እነዚህን ሰፊ የታክስ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል። ይህ የሆነው የብድሩ ቅድመ ሁኔታ የሀገሪቱን የውስጥ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ስለሚጠይቅ እንደሆነም ተብራርቷል።

በዚህም መሠረት የነዳጅ ድጎማው ሙሉ በሙሉ ተነስቶ ዋጋው በገበያ እንዲወሰን የሚደረግ ሲሆን፣ በሪል እስቴት፣ በመኪና ባለቤትነት እና በተለያዩ ምርቶች ላይ አዳዲስ ቀረጦች የሚጣሉ ይሆናል ተብሏል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአንድ ወቅት የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (IMF) ብድር ቀላልነት ሲገልጹ «ከአይ.ኤም.ኤፍ መበደር ከእናት መቀነት እንደ መፍታት ነው...» ማለታቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ የዚያ "ቀላል" ብድር ዋጋና ቅድመ-ሁኔታዎች በዜጎች ኪስ ላይ እየፈጠሩት ያለው ጫና ቀላል አለመሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።

በየጊዜው የሚጨመሩ ታክሶች፣ አዳዲስ ቀረጦች እና የዋጋ ንረቱ «ለመሆኑ ለብድር ተብሎ በሕዝብ ላይ ታክስ መጫን ተለመደ እንዴ?» የሚል ጥያቄ አስነስቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቱ እየተተገበሩ ያሉ የፖሊሲ ለውጦች (የኤክሳይዝ ታክስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማሻሻያዎች እና የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪዎች) ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ ክፉኛ እየፈተኑት ይገኛሉ።

ከውጭ ምንዛሬ ተመን መለቀቅ ጋር ተዳምሮ የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

Seledadotio
Seledadotio
19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.