ኢራን የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤን በቋሚነት እንደምትቆጣጠር አስታወቀች
የኢራን ባለስልጣናት በአሜሪካ እና በእስራኤል የተጀመረው ጦርነት ከመነሻው አንስቶ የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤን "ቀይ መስመር" ወይም ሊጣስ የማይገባ ወሳኝ ጉዳይ አድርገው ሲገልጹት ቆይተዋል። ብሪጋዲየር ጄኔራል ኢብራሂም ዞልፋጋሪ በሰጡት መግለጫም ይህንኑ አቋም የሚያጠናክር ነው።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የኢራንን የኃይል ማመንጫና ማከፋፈያ መሰረተ-ልማቶች ስለማጥቃት በተደጋጋሚ መናገራቸው፣ ይህ መግለጫ የተሰጠዉ በወሳኝ ጊዜ እንዲሆን አድርጎታል።የወታደራዊው ዋና መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ አሜሪካ በኢራን መሰረተ-ልማቶች ላይ ተጨማሪ ጥቃቶችን ብትፈጽም፣ ኢራንም በአካባቢው የሚገኙ መሰረተ-ልማቶች ላይ የአጸፋ ጥቃት ትሰነዝራለች። ኢራን እስካሁን ይህን ያላደረገችው አቅም ስለሌላት ሳይሆን፣ የመታቀብ ፖሊሲ ስላላት ነው ፤ ነገር ግን አሜሪካ እንደዚህ አይነት ጥቃቶችን ከፈጸመች ያ የመታቀብ ፖሊሲ ያበቃል ሲል መስሪያ ቤቱ አክሏል።
የኢራን ዋና ተደራዳሪ እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ባጌር ጋሊባፍ እንደተናገሩት፣ የኢራን ብሔራዊ ደህንነት በሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤ ውስጥ "የኢራን አሰራሮችን" በመጠበቅ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ "ጠላት" ይህንን በኃይል ለማዳከም እየሞከረ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።ኢራናውያን የሚያወሩት ስለ ሆርሙዝ ጊዜያዊ ቁጥጥር አይደለም፤ ይልቁንም ለዓለም የሚያስተላልፉት መልእክት ኢራን በዚህ ስትራቴጂካዊ የውሃ መስመር ላይ ዘላቂ ቁጥጥር እና ሉዓላዊነት እንዲኖራት ነው። ይህ ደግሞ በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ላለው ውጥረት ዋና ምክንያት ነው።
Seledadotio

20 days ago