Logo
YenetaTube
ዛምቤዚ ባህር ሰጥመዋል የተባሉ ኢትዮጵያዉያን በህይወት ተገኙ

አምስት ኢትዮጵያዉያን ግን እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም!

ባለፈዉ ሰኞ ማታ ከዛምቢያ ወደ ቦትስዋና ለመሻገር ሲሞክሩ ዛምቤዚ ወንዝ ዉስጥ ሰጥመዋል ተብለዉ ከተጠረጠሩት 10 ኢትዮጵያውያን ወንዶች መካከል አምስቱ በሕይወት መገኘታቸዉን አንድ የዛምቢያ ድረ-ገጽ ዘገበ። News Diggers የተባለዉ አምደ-መረብ የዛምቢያን ደቡባዊ ግዛት ፖሊስ አዛዥን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የቀሩትን ሰዎች የመፈለግ እና የምርመራ ሥራው ቀጥሏል።

ቻርለስ ናምቡላ የተባሉ የኢሚግሬሽን ኦፊሰር፣ በበኩላቸዉ ሐምሌ 7 ቀን ባቀረቡት ሪፖርት፤ 10 ኢትዮጵያውያን ወንዶች ሐምሌ 6 ቀን ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ከዛምቢያ ወደ ቦትስዋና በህገ-ወጥ መንገድ ለመሻገር ሲሞክሩ ሙዋንጋ በተባለ መንደር አቅራቢያ ዛምቤዚ ወንዝ ዉስጥ ሰጥመዋል ተብሎ እንደተጠረጠረ አስታውቀው ነበር።

ከመስመጥ ከተረፉት ስደተኞቹ ሁለቱ መያዛቸዉን አስታዉቀዉም ነበር።ሃገሪቱ ደቡባዊ ግዛት ፖሊስ አዛዥ ትናንት ረቡዕ በሰጡት መግለጫ ደግሞ ሰምጠዋል ከተባሉት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች መካከል አምስቱ መገኘታቸዉን የሚያሳይ የመረጃ ለ ፖሊስ ደርሶታል ብለዋል።

DW Amharic

21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.