Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት እና ዳግም የጣለችውን የባህር ላይ እገዳ ተከትሎ፣ ባህሬን የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ሳይረን ማሰማቷን የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ "የማስጠንቀቂያ ሳይረን ተሰምቷል" ያለ ሲሆን፤ "ዜጎች እና ነዋሪዎች ተረጋግተው በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ስፍራ እንዲያመሩ" ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
በተመሳሳይ ወቅት ኩዌት በበኩሏ፣ የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል "ጠላት" ከተባሉ የኢራን አጥቂ ድሮኖች ጋር ውጊያ እያደረገ መሆኑን አስታውቃለች።

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.