Logo
Getu Temesgen
በሚኒሶታ የሚገኘው የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የእሳት አደጋ ተጎዳ
#ethiopia | በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ሮዝማውንት (Rosemount) ከተማ የሚገኘው የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በድንገት በተከሰተ የእሳት አደጋ ክፉኛ ተጎድቷል።

አደጋው የደረሰው ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. (ጁላይ 13፣ 2026) የቅድስት አርሴማ ወርሃዊ በዓል የቅዳሴ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሲሆን፣ እሳቱ በህንጻው ጣሪያና በውስጣዊ ክፍሎች ላይ በፍጥነት ተዛምቶ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በርካታ የእሳት አደጋ መከላከያ ቡድኖች እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ ቢያደርጉም፣ በህንጻው ላይ የደረሰው ውድመት እጅግ ከባድ መሆኑ ተገልጿል። በአደጋው ወቅት በህንጻው ውስጥ ሰው ባለመኖሩ የሕይወት መጥፋትም ሆነ የአካል ጉዳት አልተመዘገበም።

በሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በአደጋው ቦታ በመገኘት ለደብሩ ካህናት፣ ለሰበካ ጉባኤ አባላትና ለምዕመናን አባታዊ ማጽናኛ ሰጥተው፣ ቤተክርስቲያኑን በድጋሚ ለማቋቋም በአንድነት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ቤተክርስቲያን በቅርቡ ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ተገዝቶ፣ ለምዕመናን አገልግሎት መስጠት የጀመረ በመሆኑ አደጋው የበለጠ አሳዛኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

በበኩላቸው የአካባቢው ፖሊስና የእሳት አደጋ መርማሪዎች የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ CBS Minnesota (WCCO-TV)፣ FOX 9 Minneapolis–St. Paul፣ KARE 11 News

23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.