(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ፔንታጎን በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት መሰንዘር ዳግም መጀመሩን ለህግ አውጪዎች በይፋ ማሳወቃቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ።
ሲቢኤስ እና ፖሊቲኮ ሚዲያዎች እንደዘገቡት፣ ትራምፕ ጁላይ 10 ለኮንግረስ በጻፉት ደብዳቤ፣ ጁላይ 7 ዳግም የተጀመረው ይህ ጥቃት "በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ አሜሪካውያንን እና የአሜሪካን ጥቅሞች ለመጠበቅ ካለብኝ ኃላፊነት ጋር የሚጣጣም ወታደራዊ እርምጃ ነው" ብለዋል። በዚሁ ደብዳቤ ላይ የቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች "ውስን፣ የተመጠኑ፣ የታቀዱ እና የሲቪል ሰለባዎችን (በንጹሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት) ለመቀነስ ታስበው የተፈጸሙ" መሆናቸው ተገልጿል።
በአሜሪካው የ1973ቱ የጦርነት ስልጣን ውሳኔ (War Powers Resolution) ህግ መሰረት ፕሬዝዳንቱ ማንኛውንም ወታደራዊ እርምጃ በጀመሩ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለኮንግረስ ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ህጉ በተጨማሪም የኮንግረስ ይሁንታ (ማጽደቂያ) ሳይኖር የተጀመረ ማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ በ60 ቀናት ውስጥ መቆም እንዳለበት ይደነግጋል።
አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘር የጀመረችው ፌብሩዋሪ 28 ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በኤፕሪል ወር ላይ በተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ሆኖም አሜሪካ የኢራን ወደቦችን እስከመዝጋት የደረሰችበት ተከታታይ የአጸፋ ጥቃቶች ቀጥለው ቆይተዋል።
የመጀመሪያው የ60 ቀናት የህግ ገደብ ሜይ 1 ላይ ያበቃ ቢሆንም፣ ትራምፕ "በተኩስ አቁም ስምምነቱ ምክንያት የ60 ቀኑ ገደብ አይተገበርም" በማለት የኮንግረስን ፈቃድ ሳይጠይቁ ቀርተዋል። ይህንንም ተከትሎ፣ ሁለቱም የኮንግረስ ምክር ቤቶች ትራምፕ የአሜሪካን ጦር ከኢራን ጋር ካለው ግጭት እንዲያስወጡ የሚያዝ የጦርነት ስልጣን ውሳኔ አሳልፈዋል።

3 months ago