Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ሊያባርሩ መሆኑን አስታወቁ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ዛሬ በቴሌግራም ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልእክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሊያ ስቪሪደንኮን ጨምሮ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ ከፍተኛ ሹምሽር ለማድረግ መወሰናቸውን ገለፁ፡፡ በመልእክታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዚህ ወሳኝ ወቅት ለነበራቸው አመራር ጥልቅ አድናቆት እንዳላቸው የጠቀሱት ዘለንስኪ በጉዳዩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ማወያየታቸውን አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተነሱ በኋላ በዲፕሎማሲው መስክ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ የሚመደቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹አሁን አገራችን ያለባትን ፈተና ከግምት ውስጥ በማስገባት በውስጥ ያለውን የመንግስት አሰራራችንን ማዘመንና ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ውስጥ ለጦርነቱ የሚቀርበውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማሳደግና ለመጪው ክረምት ዝግጅት ማድረግም ግድ ነው›› ያሉት ዘለንስኪ ከጠቅላይ ሚኒስትሯ በተጨማሪ ሌሎች ሚኒስትሮችም ከስልጣናቸው እንደሚነሱ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ይህ ሹም ሽራቸው በይፋ እንዲፀድቅ የፓርላማው ይሁንታ የሚያስፈልገው ሲሆን በዛሬ መልእክታቸውም ‹‹ከፓርላማው አባላት ጋር በመሆን በዩክሬይን መንግስት ውስጥ ጠንካራ ለውጦችን እናደርጋለን ብዬ እገምታለሁ›› ብለዋል፡

23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.