Logo
SeledaPost
የማይሞተው ብቸኛው የምድር ፍጡር

እርጅናን በመቀልበስ የሕይወት ዑደቱን ወደ ሕፃንነት በመመለስ ለዘላለም መኖር የሚችል “የማይሞት” አስገራሚ ፍጡር በባሕር ጥልቀት ውስጥ መገኘቱ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶችን አስደምሟል።

“ቱሪቶፕሲስ ዶርኒ” (Turritopsis dohrnii) የተባለውና በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ይህ የጄሊፊሽ (Jellyfish) ዝርያ በሕይወት ዘመኑ ላይ አደጋ፣ በሽታ ወይም እርጅና ሲደቅንበት የራሱን ሴሎች ሙሉ በሙሉ በማደስ ወደ መጀመሪያው የፅንስ (Polyp) ደረጃ የመመለስ አስደናቂ የተፈጥሮ ብቃት አለው።

ይህ ማለት ፍጡሩ ሲያረጅ ከመሞት ይልቅ ልክ እንደገና ተወልዶ ወደ ሕፃንነቱ ይመለሳል፤ ይህንን ሂደት ደግሞ ሳይሞት ለዘላለም ደጋግሞ ማከናወን ይችላል።

ተመራማሪዎች የዚህን ፍጡር የዲኤንኤ (DNA) ምስጢር ለመፍታት ሌሊትና ቀን እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን፣ ግኝቱ ለሰው ልጅ የእርጅና መከላከያ እና የካንሰር ሕክምና ምርምር ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ በመሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያና በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

Seledadotio
Seledadotio
24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.