ከጀሞ 1 ወደ ጀሞ 3 የሚወስደው መንገድ ከነገ ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ ይሆናል ተባለ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በላፍቶ ሆስፒታል አካባቢ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል አስቸኳይ የቦክስ ከልቨርት ግንባታ መጀመሩን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ እንደገለጸው የግንባታ ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ከነገ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በመሆኑም ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በላፍቶ ሆስፒታል ጀርባ በኩል እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል።
እንዲሁም ከጀሞ ሦስት አደባባይ ወደ ጀሞ አንድ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በሀጫሉ ሁንዴሳ ጎዳና በኩል በቫርኔሮ አደባባይ አድርገው እንዲጓዙ መመሪያ ተሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የግንባታ ሥራው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አሽከርካሪዎች በተለዋጭ መንገዶች በመጠቀም የተለመደውን ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
Seledadotio

26 days ago