ሰሞኑን በሚኒሶታ የተካሄደው የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌስቲቫል ላይ በተለይ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት ለኮምዩኒቲያችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉት የሚኒሶታ ግዛት የህግ አውጪ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሰማካብ ሁሴን (State Representative Samakab Hussein) ፣ የ2026ቱን የህግ አውጪ የስራ ዘመን በይፋ ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል። የህዝብ ተወካዩ ባወጡት መግለጫ በምክር ቤቱ ውስጥ የተወካዮች ቁጥር እኩል በሆነበት ታሪካዊ እና ፈታኝ አጋጣሚ ውስጥም ቢሆን፣ ለሴንት ፖል ከተማም ሆነ ለመላው የሚኒሶታ ግዛት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ማበርከት በመቻላቸው ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸዋል።
አሁንም ቢሆን ከፊታቸው የሚጠብቁ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ተወካዩ... ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማምጣት ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ መስራት በመቻላቸው እጅግ እንደሚኮሩ አክለው ተናግረዋል።
የህዝብ ተወካዩ በቀጣይ የሚያደርጓቸውን ተግባራት ይበልጥ አቅጣጫ ለማስያዝ እንዲረዳቸው፣ ነዋሪዎች ጥቂት ጊዜ ወስደው ያዘጋጁትን የህግ አውጪ የዳሰሳ ጥናት እንዲሞሉ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም እንደሁልጊዜው ሚኒሶታን ይበልጥ የተሻለች ለማድረግ የሚያስችሉ ማናቸውም ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም አዳዲስ ሀሳቦች ያላቸው ዜጎች ቢሮአቸውን በማነጋገር እንዲያሳውቋቸው በአክብሮት ጋብዘዋል።
ለኮምዩኒቲያችን ይጠቅማል ብላችሁ የምታስቡትን በሚከተለው ድረገጽ ገብታችሁ ብትሞሉ ይመከራል። እንሳተፍ፣ ለኛ ጉዳይ ሌሎች እንዲወስኑልን አንፍቀድ! https://www.surveymonkey.c...

26 days ago