"ከኢራን ጋር የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት አብቅቷል"
- ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
#ethiopia | በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት በድጋሚ ተባብሷል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቱርክ አንካራ በተካሄደው የኔቶ መሪዎች ጉባኤ ላይ፣ ከኢራን ጋር የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት "አብቅቷል" ሲሉ በይፋ አስታውቀዋል።
ትራምፕ ይህን ያሉት፣ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በንግድ መርከቦች ላይ ለተፈጸመ ጥቃት ምላሽ በመስጠት ከ80 በላይ የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎችን፣ የራዳር ጣቢያዎችንና ፈጣን የባህር ጀልባዎችን ኢላማ ማድረጉን ተከትሎ ነው።
ፕሬዝዳንቱ ከኢራን ጋር የሚደረግ ድርድር "የጊዜ ማባከን" መሆኑን በመግለጽ፣ የኢራን መሪዎችን "ውሸታሞችና አታላዮች" ሲሉ በጥብቅ ተችተዋል።
በሌላ በኩል ኢራን በአሜሪካ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን ሲገልጽ፣ በአገሪቱ ላይ የተጣለው የዘይት ሽያጭ ማዕቀብ መመለሱም ውጥረቱን ይበልጥ አባብሶታል። በዚሁ ጊዜ የኢራን የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሀመድ ባቀር ቃሊባፍ፣ "የማስፈራራትና የጫና ዘመን አብቅቷል፤ እኛ በፍጹም አንንበረከክም" በማለት ሀገራቸው ለውጫዊ ጫና እንደማትገዛ ገልጸዋል።
የሁለቱ ሀገራት ግጭት እየተባባሰ በመሄዱ፣ በቀጣናው የደህንነት ሁኔታና በዓለም የኃይል ገበያ ላይ አዲስ ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል።
#አሜሪካ #ኢራን #ትራምፕ #የዓለምዜና #breakingnews

28 days ago