Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የህንዱ የፊልም ኮከብ አሚታብ ባቻን ስለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን የሰጠው አስተያየት መነጋገሪያ ሆነ፡፡ አንጋፋው የቦሊውድ የፊልም ኮከብ አሚታብ ባቻን የፊፋ 2026 አለም ዋንጫን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጨው መልእክት ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ይህ የህንድ ኮከብ በኤክስ ገፁ ላይ ትላንት የፃፈው አስተያየት የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን የሚመለከት ነው፡፡ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ቋሚ 11 ተሰላፊዎች ውስጥ 10ሩ ጥቁሮች መሆናቸውንና አንድ ብቻ ነጭ መገኘቱን ጠቅሶም ‹‹ይህ የጥቁርን ሀይል ያሳያል›› በማለት የክንድ ምልክትን የሚያሳይ ኢሞጂ አያይዞ አስቀምጦ ነበር፡፡

ይህ ልጥፉ ትላንት ምሽት እንደተቀመጠ ወዲያውኑ ቫይራል በመሆን መነጋገሪያ ለመሆን ችሏል፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም የተለያየ ግብረ መልስ ሰጥተውታል፡፡ ጥቂቶች ተዋናዩ የግል ምልከታውን እንዳሰፈረ በመግለፅ ድጋፋቸውን ቢሰጡትም በርካቶች ግን ‹‹አስፈላጊ ያልሆነ ዘረኝነትን የሚያንፀባርቅ ነው›› በማለት ተቃውሞ አቅርበውበታል፡፡ እንዲሁም የተጨዋቾቹን የፈረንሳይ ማንነት ችላ ያለ አስተያየት አድርገው የጠቀሱም አሉ፡፡

በርካታ አስተያየት ሰጪዎች የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አባላት የዘር ግንዳቸው ከየትም የሚቀዳ ቢሆን አሁን የሚወክሉት ፈረንሳይን መሆኑን ጠቅሰው ይህም የአገሪቱን ህብረ ብሄራዊነት ባህል እንደሚያንፀባርቅ አስረድተዋል፡፡

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.