በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው የደመቀው ሃላንድ…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ ምርጥ ጊዜ እያሳለፉ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ኤርሊንግ ሃላንድ፡፡
ኖርዌይ 4ኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን እያደረገች ሲሆን÷ የብሔራዊ ቡድኑ ኮከብ ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ ደግሞ በመድረኩ የመጀመሪያ ተሳትፎውን እያደረገ ይገኛል፡፡
ኖርዌይ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 1938 ፈረንሳይ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ነበር ፤ በወቅቱ ገና በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ከውድድሩ መሰናበቷ ይታወሳል፡፡
ሁለተኛ ተሳትፎዋን ያደረገችው ደግሞ በፈረንጆቹ 1994 አሜሪካ ባዘጋጀችው መድረክ ሲሆን÷ በዚህ ጊዜም ከምድብ ማለፍ አልቻለችም ነበር፡፡
በፈረንጆቹ 1998 በፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ ለሦስተኛ ጊዜ በመድረኩ የተገኘችው ኖርዌይ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ነበር ከውድድሩ የተሰናበተችው፡፡
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ኖርዌይ ከ28 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ወደ መድረኩ እንድትመለስ ትልቁን አስተዋጽኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች መካከል ሃላንድ ቀዳሚው ነው፡፡
ሀገሩ ኖርዌይ ከ28 ዓመታት በኋላ በተመለሰችበት የዓለም ዋንጫ ውድድር ሩብ ፍጻሜውን ስትቀላቀል ሃላንድ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡ኖርዌይም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ውድድር ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡
ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ከሀገሩ ኖርዌይ ጋር አስደናቂ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡
ተጫዋቹ እስካሁን ባደረጋቸው የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ሃላንድ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ከሜሲ በአንድ ግብ በማነስ ከከሊያን ምባፔ እኩል 7 ግቦችን በማስቆጠር ለወርቅ ጫማው እየተፋለመ ነው፡፡
የ25 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ከሀገሩ ኖርዌይ ጋር በውድድሩ የሚቆይ ከሆነ ለወርቅ ጫማው የሚያደርገውን ፉክክር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡
ሃላንድ የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድንን ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ እያገለገለ ሲሆን÷ እስካሁን ድረስ 54 ጨዋታዎችን አድርጎ 62 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
በዚህም የምንጊዜውም የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃውን እየመራ ይገኛል፡፡በተጨማሪም ስድስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለብሔራዊ ቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ገና 25 ዓመቱ ላይ የሚገኘው ሃላንድ በቀጣይ ለኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ግቦችን በማስቆጠር የግብ መጠኑን ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በቀጣይ ኖርዌይ በሩብ ፍጻሜው ፍልሚያ ከ1966 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ሀገር እንግሊዝ ጋር በምታደርገው ጨዋታ ኤርሊንግ ብራውት ሃላንድ ተጠባቂው ተጫዋች ነው፡፡
ኖርዌይ በቀጣይ ከእንግሊዝ ጋር የምታደርገውን ጨዋታ አሸንፋ ቀጣዩን ዙር የምትቀላቀል ከሆነ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ መድረክ ግማሽ ፍጻሜውን የምትቀላቀል ይሆናል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

28 days ago