Logo
FastMereja
አካባቢን የማይጎዱ ወይም የአካባቢን ብክለት የሚያስቀሩ የንግድ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ለተሻለ ውጤት እንዲበቁ የሚያግዝ ፕሮጀክት ተጀመረ።

ይኸው ለስራ ፈጣሪ ወጣቶች ይህ ትልቅ እድል የተባለለት የሥልጠና እና የአቅም ግንባታ ፕሮግራም የተሰናዳው በግሪን ፊውቸር አፍሪካ ነው።

ግሪን ፊውቸር አፍሪካ በ2017 ዓ.ም ጀምሮ በጀስቲሻ ሚዲያ እና በብሪቲሽ ኤምባሲ እና በተለያዩ አጋር አካላት እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ነው።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ከ300 ወጣት አመልካቾች 10 የላቁ ወጣቶች ሥልጠና ወስደው ንግዳቸውን ስለማስቀጠላቸው ተዘግቧል ።

ከተጠቃሚዎቹም ከትግራይ ቬርሚ ኮምፖስት ማዳበሪያ፣ ከአፋር ፕሮሶፒስ በሚባል ተክል ጡብ መስራት እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ከሙዝ ግንድ ወረቀት በመስራት የገንዘብ ሽልማት እና ለ6 ወር ነጻ የህግ ማማከር አገልግሎት አግኝተዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍም ከ2000 በላይ አመልካቾች ይጠበቃሉ። ከእነዚህ ውስጥ 300 ወጣቶች ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ሲሆን ከ300 ውስጥ 100 አሸናፊ ወጣቶች ሙሉ ሥልጠና ያገኛሉ ነው የተባለው ።

ነጻ የ(ማርኬቲንግ እና ብራንዲንግ፣ የህግ እና የንግድ ምዝገባእና የታክስ፣ የፋይናንስ አቀራረብ፣ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ፣ እንግሊዝኛ እና ፒች ማቅረቢያ ክህሎት) ፣ ከ6 ወር በላይ የህግ እና የንግድ ምክር ድጋፍ ፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሥልጠና ዓለም አቀፍ ንግዳቸውን እና ስራቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ፣የምስክር ወረቀት እና የከተማ ጉብኝት መርሃ ግብር ለምርጥ 10 አሸናፊዎቹ የተዘጋጁ ሽልማቶች ናቸው ።

ወጣቶች የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆንም https://greenfutureafrica.... ወይም +251-913-65-80-06 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።

ምዝገባው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የመረጃ ለውውጥ ክፍለ ጊዜው ከዩኒቨርሲቲ ጉብኝቱ በኋላ በብሪቲሽ ካውንስል ግቢ ወስጥ ይካሄዳል።

እስከ አሁን ጀስቲሻ ሚዲያ ፣ብሪቲሽ ኤምባሲ አዲስ አበባ፣ብሪቲሽ ካውንስል ኢትዮጵያ፣አዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣የኛ ማይክሮ ፋይናንስ፣ አብሌዝ ቴክኖሎጂስ፣ ቢዩ ዴሊቨሪ እና ጉለሌ ቦታኒክ ጋርደን አጋር ድርጅቶች መሆናቸው ታውቋል።

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.