Logo
Getu Temesgen
ስፔን ፖርቱጋልን 1ለ0 አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ አለፈች
#ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የ16 ቡድኖች ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስፔን በ90+1ኛው ደቂቃ በMikel Merino ያስቆጠረችው የመጨረሻ ደቂቃ ጎል ፖርቱጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ አልፋለች።

ጨዋታው በአብዛኛው የተመጣጠነና የመከላከል ፉክክር የበዛበት ቢሆንም፣ ስፔን በመጨረሻ ደቂቃዎች የፈጠረችውን እድል በመጠቀም የማሸነፊያ ጎል አስቆጥራ የሩብ ፍጻሜ ትኬቷን አረጋግጣለች።

የማሸነፊያውን ጎል ሜሪኖ በተጨማሪ ሰዓት አስቆጥሮ የፖርቱጋልን ተስፋ አጨልሟል።

በዚህ ውጤት ስፔን በሩብ ፍጻሜ ከአሜሪካ ወይም ከቤልጂየም አሸናፊ ጋር ትገናኛለች።

በሌላ በኩል የ41 ዓመቱ Cristiano Ronaldo ከፖርቱጋል ጋር ያደረገው ይህ የመጨረሻ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሊሆን ይችላል የሚሉ ግምቶች ቢኖሩም፣ ተጫዋቹ ከጨዋታው በፊት “መቼ እንደማቆም እኔ እወስናለሁ” በማለት ጉዳዩን ክፍት መተዉን ገልጿል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.