ለሐዋሳ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ተሰባሰበ
በተፈጥሮ ውበቷ የምሥራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ዕንቁ በመሆን የምትታወቀው የሐዋሳ ከተማ፣ የተፈጥሮ መስህቧን ከዘመናዊ ሰው ሠራሽ ጥበብ ጋር በማቀናጀት አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ ትገኛለች።
ይህንን የኮሪደር ልማትና ውበት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትናንት በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የማጠቃለያ መድረክ፣ ለሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሀብት ማሰባሰብ በታላቅ ስኬት ተከናውኗል።
የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፣ ለአጠቃላዩ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ 3.2 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብሩን በሕዝብ፣ በባለሀብቶችና በሐዋሳ ወዳጆች አጋርነት ለመሰብሰብ ታቅዶ አሁን ላይ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።
በዚህ የመጀመሪያ ምዕራፍ ልማት የሚከናወንባቸው ዋና ዋና አካባቢዎች፡
* የፍቅር ሐይቅ
* የአሞራ ገደል
* የአሳ ገበያ አካባቢዎች
በእነዚህ ስፍራዎች ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መስመሮች፣ የመዝናኛ ስፍራዎችና የጀልባ ማረፊያዎች በስፋት እንደሚገነቡ ከንቲባው አብራርተዋል።
"የዘራነው የትብብር ዘር ነገ የእድገት ዛፍ ይሆናል"
— ከንቲባ ጥራቱ በየነ
ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ለፕሮጀክቱ መሳካት የላቀ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ለሐዋሳ ሐይቅ ልማት የተደረገው አስተዋጽኦ የከተማዋን የወደፊት ዕድገት የሚያፋጥን ታሪካዊ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፣ ያበረከተው እያንዳንዱ መዋጮ ወደ ውብ የሐይቅ ዳርቻ፣ ወደ አረንጓዴ ሕዝባዊ ስፍራዎች፣ ወደ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ወደ ሰፊ የሥራ ፈጠራ ዕድል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
"የከተማ አስተዳደሩ የተጣለበትን አደራ በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በከፍተኛ ታማኝነት በመወጣት ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ በትጋት ይሠራል::"
ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ሐዋሳን የአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝምና የኮንፍረንስ ከተማ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የማድረግ ራዕይን እውን ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የገለጹት አቶ ጥራቱ፣ ባለሀብቶች ወደ ሀዋሳ በመምጣት እውቀትና ሀብታቸውን ተጠቅመው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

1 month ago