(ዘ-ሐበሻ ዜና) ማንችስተር ሲቲ ኤንዞ ማሪስካን በአሰልጣኝነት ቀጠረ፡፡ ማንችስተር ሲቲ ፔፕ ጋርዲዮላን የሚተካውን አሰልጣኝ ዛሬ ይፋ ያደረገ ሲሆን እሱም ጣሊያናዊው ኤንዞ ማሬስካ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ማሬስካ ከክለቡ ጋር የ3 አመት ኮንትራት መፈራረሙ ተገልጿል፡፡
ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ባለፈው ጃንዋሪ ወር ከቼልሲ ጋር የተለያየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ማንችስተር ሲቲ አሰልጣኙን ያስፈረመው ከቼልሲ ጋር ስምምነት አድርጎ ነው፡፡ አንዳንድ ዘገባዎች ሲቲ አሰልጣኙን ለመውሰድ 17 ሚሊዮን ፓውንድ ለቼልሲ መክፈሉን በመዘገብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ማሬስካ ለማንችስተር ሲቲ እንግዳ አይደለም፡፡
ከዚህ ቀደም የክለቡን የወጣቶች ቡድን ያሰለጠነ ከመሆኑም በላይ እ.ኤ.አ በ2018/19 የውድድር ዘመን ሲቲ 3 ዋንጫዎችን ሲያገኝ የጋርዲዮላ ረዳት ሆኖ ሰርቷል፡፡ አዲስ ሀላፊነቱን በተመለከተ ሲናገር ‹‹ማንችስተር ሲቲ በደምብ የማውቀው ክለብ ነው፡፡ ይህንን ክለብ ለማሰልጠን መቻሌ ለእኔ ትልቅ አድል ነው፡፡ በብቃቴና ችሎታዬ ላይ እምነት አሳድረው ይህንን ስራ ለሰጡኝ በሙሉ አመሰግናለሁ›› ብሏል፡፡

1 month ago